English blog post: https://sdotblog.seattle.gov/2022/02/16/dont-block-the-box-traffic-cameras/
የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እና የሲያትል ፖሊስ መምሪያ (SPD) አዲስ የትራፊክ ካሜራዎችን ለመጨመር ስምንት ቦታዎችን መርጠዋል። እነዚህ የየሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እና የሲያትል ፖሊስ መምሪያ (SPD) በመሃል ከተማ ሲያትል ዙሪያ ባሉ ስምንት አካባቢዎች ላይ አዲስ የትራፊክ ካሜራዎችን ማብራት ይጀምራሉ። እነዚህ የትራፊክ ካሜራዎች በሕገ-ወጥ መንገድ በአውቶቡስ መስመሮች የሚነዱ ወይም የእግረኛ ማቋረጫዎችን እና የመስቀለኛ መንገዶችን የሚዘጉ መኪኖችን ፎቶ ያነሳሉ። እነዚህ ካሜራዎች የህዝብን ደህንነት ለማሻሻል፣ የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ፣ የሕዝብ መጓጓዣ መንቀሳቀስ እንዲቀጥል እና የአካል ጉዳተኞችን ተንቀሳቃሽነት ለመጨመር ይረዳሉ።
ከ2022 ጀምሮ፣ አዲሶቹ የትራፊክ ካሜራዎች ህጉን የሚጥሱ ተሽከርካሪዎችን የኋላ ታርጋ ፎቶግራፍ ያነሳሉ። አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዝ፣ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይላክለታል። ከዚያ በኋላ ለሚደረጉ ማናቸውም የሲያትል ከተማ እነዚህ ካሜራዎች በመጋቢት ወር መሥራት እና ማስጠንቀቂያዎችን መስጠት ይጀምራል። ህዝቡ ከለውጦቹ ጋር እንዲላመድ ጊዜ ለመስጠት እና ስርዓቱን በየቦታው ለመፈተን ካሜራዎቹ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ቀስ በቀስ ይበራሉ።
ህጉን የሚጥሱ ተሽከርካሪዎችን ታርጋ አዲሶቹ የትራፊክ ካሜራዎች ፎቶግራፍ ያነሳሉ። አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዝ፣ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይላክለታል። ከዚያ በኋላ ለሚደረጉ ማናቸውም ጥሰቶች፣ የ$75 ዶላር ትኬት ቅጣት በፖስታ ይላክላቸዋል።
ሁሉም አካባቢዎች ግልጽ ምልክቶች እና የእግረኛ መንገድ ምልክቶች ይኖራቸዋል። የእግረኛው መንገድ ምልክቶች የመስቀለኛው መንገድ የት እንደሚጀመር የሚያመለክቱ ነጭ መስመሮችን ያጠቃልላል። ቀይ ቀለም ለአውቶቡሶች ብቻ የተገደቡ መስመሮችን ያሳያል።
መብራቱ ወደ ቀይ ከተቀየረ በኋላ የሚያሽከረክሩት ሰዎች የእግረኛ ማቋረጫዎችን እና መስቀለኛ መንገዶችን እንዳይዘጉ ለመከላከል ካሜራዎች በተጨናነቁ (ስራ በሚበዛባቸው) አራት መስቀለኛ መንገዶች ላይ እየተገጠሙ ነው። አሽከርካሪዎች ዘልቀው እንዲያልፉ ጥርት ያለ መንገድ ሳይኖራቸው ወደ መስቀለኛ መንገድ መግባታቸው ህገ-ወጥ ነው። መስቀለኛ መንገዶችን እና የእግረኛ ማቋረጫዎችን መዝጋት ህገ-ወጥ እና አደገኛ ባህሪ ነው። የአደጋዎች ስጋትን ይጨምራል እና በእግረኛ ማቋረጫ ላይ ያሉ ሰዎች በደህና መንገዱን እንዳያቋርጡ ይከላከላል። ይህ በተለይ ለአካል ጉዳተኞች አደገኛ ነው። ዓይነ ስውራን፣ ተሽከርካሪ ወንበሮችን የሚጠቀሙ፣ ወይም ሌላ የመንቀሳቀሻ አስፈላጊነት ያላቸው ሰዎች ወደ እግረኛው መንገድ የሚመለሱበት አስተማማኝ መንገድ በሌለበት መሀል መንገድ ላይ በጉዳት ውስጥ ሊቀረቀሩ ይችላሉ። የመስቀለኛ መንገዱ መዘጋት መጨናነቅን ይጨምራል እናም ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ይከለክላል እና ትራፊክን ወደ መቆም ያደርሳል።
ሌሎች ካሜራዎችም ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ በነሱ ላይ እንዳይነዱ ለመከላከል በአምስት ቦታዎች ላይ ያሉትን የአውቶቡስ መስመሮችን ይቆጣጠራሉ። ይህ የሕዝብ መጓጓዣ ስርዓታችንን የበለጠ አስተማማኝ እንዲሆን እና ሁሉንም ለመጥቀም አውቶቡሶች እንዲንቀሳቀሱ ይረዳል። አውቶቡሶች ከግለሰብ መኪኖች ይልቅ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ያጓጉዛሉ። እያንዳንዱ ሰው በአውቶቡስ ተጓዘ ማለት በመንገድ ላይ አንድ መኪና ተቀንሰዋል ማለት ነው። ይህ ሁሉም ሰው መጨናነቅን እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ መርዳት የሚችልበት እጅግ በጣም አስፈላጊ መንገድ ነው።
አዲሶቹ ካሜራዎች በመሃል ከተማ ሲያትል፣ ደቡብ ሌክ ዩኒየን፣ ቤልታውን፣ ፓይኒር አደባባይ፣ እና የስቴት መስመር 99 ውስጥ ባሉ ስምንት ቦታዎች ላይ ይገጠማሉ። እነዚህ ቦታዎች የተመረጡት ሰዎች በሕገ-ወጥ መንገድ የመስቀለኛ መንገዶችን፣ የእግረኛ ማቋረጫዎችን በመዝጋት፣ ወይም በሕዝብ መጓጓዣ መንገድ ላይ የማሽከርከር ታሪክ ስላላቸው ነው።
የ ዋሽንግተን ስቴት ህግ አውጭው አካል የአውቶቡስ መስመር እና የመስቀለኛ መንገድ ጥሰቶችን ለማስፈጸም የካሜራዎች መጠቀምን በ2020 ፈቀደ።
ሰዎች የመንገድ ህግጋቱን ማወቅ እና ትኬቶችን መቀበል እንዲያስወግዱ ጊዜ እንዲኖራችው ለማረጋገጥ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) አዲሱን የካሜራ መገኛ ቦታዎች እና ምልክቶች የሚገጠሙባችውን በህዳር 2021 አሳውቋል። የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ይህንን ማስታወቂያ በ10 ቋንቋዎች አሳትሞታል፣ እና አስታዋሾችን በማህበራዊ ሚዲያ፣ ማህበረሰብን መሠረት ካደረጉ ድርጅቶች ጋር እና በህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያዎች ማካፈሉን ይቀጥላል።
በስቴት ህግ መሰረት፣ ከትራፊክ ካሜራዎቹ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለብስክሌት እና ለእግረኞች ደህንነት የሥራ ዕቅዶች እንዲሆን ወደ ዋሽንግተን ትራፊክ ደህንነት ኮሚሽን ፈንድ ይሄዳል። እንዲሁም የተሰበሰበው ገንዘብ በሲያትል ውስጥ ለአካል ጉዳተኞች የደህንነት እና የተንቀሳቃሽነት ማሻሻያዎችን ለመገንባት ጥቅም ላይ ይውላል። የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT) በሲያትል መስቀለኛ መንገዶች ላይ ይበልጥ ተደራሽ የሆኑ የእግር ጉዞ ምልክቶችን ለመገንባት ይህንን ገንዘብ ሊጠቀምበት ያቅዳል። እነዚህ ምልክቶች ሰዎች መንገዱን ለማቋረጥ ደህና መሆኑን እንዲያውቁ የሚንቀጠቀጡ እና ድምጽ የሚያሰሙ በእጅ የሚጫኑዋቸው አዝራሮች አሏቸው።
አዲሶቹ ካሜራዎች እንደ የትምህርት ቤት ቀጠና የደህንነት ካሜራዎች ባሉ ሌሎች የሲያትል ክፍሎች እንደ የፎቶ ማስፈጸሚያ አዲሶቹ ካሜራዎች እንደ የትምህርት ቤት ቀጠና የደህንነት ካሜራዎች ባሉ፣ ሌሎች የሲያትል ክፍሎች እንደ የፎቶ ማስፈጸሚያ ካሜራዎች ይሰራሉ። እነዚህ ካሜራዎች የፖሊስ መኮንኖች በሌሎች የህዝብ ደህንነት ፍላጎቶች ላይ እንዲያተኩሩ ስለሚረዳ፣ የትራፊክ ህጎችን ለሚጥሱ ሰዎች ትኬቶችን ይሰጣሉ። ካሜራዎቹ ትኬቶች መስጠትን የበለጠ ወጥ እና ፍትሃዊ ያደርጉታል።
ግላዊነትን ለመጠበቅ፣ ካሜራዎቹ የተሽከርካሪ ታርጋዎችን ብቻ እንጂ በመኪናው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ፎቶ አያነሱም። ፎቶዎቹ በአውቶቡስ መስመር ላይ መንዳት እና መስቀለኛ መንገዶችን እና የእግረኛ ማቋረጫዎችን የመዝጋት ህጎችን ለማስከበር ብቻ ያገለግላሉ። ለሌላ የህግ አስከባሪነት ድርጊት የታሰቡ አይደሉም።