Find Posts By Topic

አዲስ የራይድ ናው (Ride Now) ፕሮግራም ለአረጋውያን (65+ ዓመት) እና ለአካል ጉዳተኞች ነፃ እና ቅናሽ የመጓጓዣ ጉዞዎችን እና ሌሎች የሀገር ውስጥ ጉዞዎችን ያቀርባል – የበለጠ ይወቁ እና ብቁ መሆንዎን ይወቁ!


Please note: you can return to the English version of this blog post, by clicking here.


በ2021 በሲያትል ውስጥ የሕዝብ መጓጓዣ አማራጮችን ለማስተዋወቅ እንዲረዳቸው የሕዝብ መጓጓዣ ተኮር የመስክ ጉብኝት ያደረጉት ከሌክ ሲቲ እና ከደቡብ ፓርክ የአረጋውያን ማእከላት የመጡ የሲያትል ነዋሪዎች ፎቶ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
በ2021 በሲያትል ውስጥ የሕዝብ መጓጓዣ አማራጮችን ለማስተዋወቅ እንዲረዳቸው የሕዝብ መጓጓዣ ተኮር የመስክ ጉብኝት ያደረጉት ከሌክ ሲቲ እና ከደቡብ ፓርክ የአረጋውያን ማእከላት የመጡ የሲያትል ነዋሪዎች ፎቶ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

_______

ማጠቃለያ:

  • በተለይ ለአረጋውያን (65+ ዓመት) እና ለአካል ጉዳተኞች እና ተንከባካቢዎቻቸው – በሕዝብ ማመላለሻ ብቻ ለመድረስ አስቸጋሪ ለሆኑ ጉዞዎችን ወደ ሕዝብ ማመላለሻ ጣቢያዎች እና ሌሎች በአቅራቢያው ባሉ መዳረሻዎች በነጻ እና በተቀነሰ ዋጋ ለማቅረብ ራይድ ናው (Ride Now) የተባለ አዲስ የሙከራ ፕሮግራም እያስጀመርን ነን።
  • ብቁ የሆኑ የማህበረሰብ አባላት ለመሳፈር የሚጠቀሙበትን $20 ዶላር ቫውቸሮችን ከየሎው ካብ፣ ከኡበር ወይም ከሊፍት ይቀበላሉ።
  • ብቁ የሆኑ ተሳፋሪዎች እንደ ወረቀት ቫውቸሮች ወይም ዲጂታል የማስተዋወቂያ መስጢራዊ አሀዞች ሊቀርቡ የሚችሉ፣ በወር እስከ 6  ቫውቸሮችን ሊጠይቁ ይችላሉ።
  • ቫውቸሮቹ ሲያትል ውስጥ ለሚጀምሩ ወይም ለሚያልቁ ጉዞዎች ናቸው፣ እና ተሳፋሪዎች ከሕዝብ ማመላለሻ ጋር ከሚገናኙ ጉዞዎች ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ሊያገኙ ይችላሉ።
  • ቫውቸሮችን ለመጠየቅ፣ እባክዎን www.seattle.gov/transportation/RideNow ይጎብኙ ወይም በ (206) 684-ROAD [7623] ይደውሉልን።
  • ቫውቸሮች በማህበረሰብ ላይ በተመሰረቱ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ሲያትል ውስጥ ካሉ ድርጅቶችም ይገኛሉ። እባክዎን የቅርብ ጊዜውን መረጃ ለማግኘት www.seattle.gov/transportation/RideNow ይጎብኙ።
  • ራይድ ናው ፓይለት ፕሮግራም በመጋቢት፣ ሚያዝያ፣ እና ግንቦት 2022 ወራት ወቅት ይሰራል። የጉዞ ቫውቸሮች ከሰኔ 1 ቀን 2022 በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  • የሙከራ ፕሮግራሙን ለሚሞክሩ ሰዎች አማራጭ የግብረመልስ ዳሰሳ እናቀርባለን፤ ይህ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ነገር ለማቅረብ እና እንዴት እንደምናቀርብ ለመወሰን ይረዳናል።

_______

እ.ኤ.አ. በ2020፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ከትራንዚት ፕላኒንግ 4 ኦል (Transit Planning 4 All)፣ የአካባቢያዊ የመጓጓዣ አገልግሎቶችን እና አማራጮችን ለማሻሻል አካታች የዕቅድ መርሃ ግብሮችን ለማዳበር እና ተግባራዊ ለማድረግ ከሚሰራው ብሄራዊ ፕሮግራም እርዳታ አግኝቷል።

ድጋፉ አካታች የሆነ፣ የሚካካስ የእቅድ ሂደት እንድናካሂድ እና ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም ለተንከባካቢዎቻቸው የመንቀሳቀስ ድጋፍ የሙከራ ፕሮግራም እንድናቀርብ አስችሎናል።

ይህ የሙከራ ፕሮግራም፣ ራይድ ናዎ (Ride Now) ተብሎ የሚጠራው፣ በነጻ ወይም የሕዝብ ማመላለሻዎችን በቅናሽ እና ሌሎች በአቅራቢያው ያሉ በሕዝብ ማመላለሻዎች ብቻ ለመድረስ አስቸጋሪ የሆኑ መዳረሻዎችን መሳፈር ለማቅረብ የታሰበ ነው። የፕሮግራም ተሳታፊዎች እነዚህን ጉዞዎች በፈለጉ ጊዜ ሊጠይቁ ይችላሉ፣ ምንም ቦታ ማስያዝ አያስፈልግም፣ እና ተደራሽ የሆነ የሎው ካብ፣ ወይም ኡበር፣ ወይም ሊፍት፣ ልክ ቤታቸው ድረስ መምጣት ይችላሉ።

የፕሮግራሙ አላማ ለእነዚህ የማህበረሰብ አባላት የበለጠ ተደራሽ፣ ምቹ እና ተመጣጣኝ የመጓጓዣ አማራጮችን ማቅረብ ነው።

አንደሚስብ ይሰማል። በትክክል ለመሳተፍ ብቁ የሚሆነው ማን ነው?

ይህ ፕሮግራም የተነደፈው አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር አብረው የሚጓዙ ተንከባካቢዎቻቸውን ለማገልገል ነው። ቫውቸሮች በሲያትል ከተማ ውስጥ በሚጀምሩ ወይም በሚያልቁ ጉዞዎች ላይ ይሰራሉ፣ እና ተሳፋሪዎች ከሕዝብ መጓጓዣ ጋር በሚገናኙት ጉዞዎች ከፍ ያለ ቅናሽ ሊያገኙ ይችላሉ። የበለጠ ዝርዝር መመሪያ በ www.seattle.gov/transportation/RideNow ላይ ይገኛል።

ብቁ ግለሰቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. አዛውንቶች: እድሜያቸው 65 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ግለሰቦች።
  2. አካል ጉዳተኞች: የአካል እና የእውቀት እክልን ጨምሮ፣ በሕዝብ ማመላለሻ መጓጓዣን የማግኘት ችሎታቸው ተፅዕኖ የሚያደርግ የማንኛውም አይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች።
  3. ተንከባካቢዎች: ከላይ ከተጠቀሱት ብቁ ተሳፋሪዎች ጋር የሚጓዙ ግለሰቦች።
የሲያትል ማህበረሰብ አባላት በ2021 የሕዝብ ማመላለሻ የመስክ ጉዟቸው በምዕራብ ሲያትል የአልካይ ሰፈር (በስተግራ) ፀሀያማ ቀን እና በአውቶቡስ በመሳፈር (በስተቀኝ) ይጓጓዛሉ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
የሲያትል ማህበረሰብ አባላት በ2021 የሕዝብ ማመላለሻ የመስክ ጉዟቸው በምዕራብ ሲያትል የአልካይ ሰፈር (በስተግራ) ፀሀያማ ቀን እና በአውቶቡስ በመሳፈር (በስተቀኝ) ይጓጓዛሉ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
በሃይል ምንጭ በሚሽከረከር ወንበር የምትጠቀም ሴት RapidRide C Line አውቶቡስ ለመሳፈር ትጠብቃለች። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
በሃይል ምንጭ በሚሽከረከር ወንበር የምትጠቀም ሴት RapidRide C Line አውቶቡስ ለመሳፈር ትጠብቃለች። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

ገባኝ። ስለዚህ አሁን ተሳፈር (Ride Now) ፕሮግራም እንዴት ነው የሚሰራው?

Graphic showing the 4 steps to take a ride with the Ride Now program.
Graphic: SDOT

የመጓጓዣ ቫውቸሮችን ከጠየቁ እና ከተቀበሉ በኋላ እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው እነሆ:

ደረጃ 1: የመሳፈር ጉዞ ያስመዝግቡ

  • ከእነዚህ ከሚገኙ ዘዴዎች በአንዱ የእርስዎን የመሳፈር ጉዞ ያስመዝግቡ:
    • ስልክ: የሎው ካብን በ (206) 622-6500 በመደወል ያስይዙ።
    • የስማርትፎን መተግበሪያ: የሎው ካብ፣ ኡበር ወይም ሊፍት በስማርትፎንዎ ላይ በመተግበሪያዎቻቸው ያስይዙ።
    • ኮምፒውተር: በኮምፒውተርዎ ወይም በታብሌቱ ላይ በድህረ-ገጻቸው አማካኝነት ኡበር ወይም ሊፍት ያስይዙ።
  • መሳፈሪያዎ መቼ እንደሚመጣ መጠበቅ እንዳለቦት መረጃ ይደርሰዎታል እና ሹፌርዎን የተወሰኑ ሁኔታዎን እንዲያስተናግዱ መጠየቅ ይችላሉ።

ደረጃ 2: ተሽከርካሪው በጊዜው ይደርሳል

  • የሚሳፈሩት የሎው ካብ፣ ኡበር ወይም ሊፍት በቅርቡ ይደርሳል፣ በተለምዶ በተጠየቀ ከ10-30 ደቂቃዎች ውስጥ።
  • የሎው ካብ የሚሽከረከር ወንበር ተደራሽ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለሚፈልጉ ተሳፋሪዎች ያቀርባል።
  • የኡበር ወይም ሊፍት ተሽከርካሪዎች በተለምዶ የቤት ሴዳን (መኪናዎች) ናቸው፣ በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር።

ደረጃ 3: አድርሰው ጣል ያድርጉ እና ይክፈሉ

  • ሹፌሩ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሕዝብ ማመላለሻ ጣቢያ ወይም በአቅራቢያዎ ካለው ሌላ መድረሻ ያወርድዎታል።
  • የተሳፈሩበትን ቅናሹን ለመተግበር የወረቀት ቫውቸርዎን ወይም የዲጂታል የማስተዋወቂያ የምስጢር አሀዝዎን ይጠቀሙ።
    • የ$20 ዶላር የመሳፈሪያ ቅናሽ ማለት ከ3 ማይሎች በታች የሆኑ ብዙ ጉዞዎችን በነጻ ወይም በጥልቅ ቅናሽ ለማድረግ የታሰበ ነው።
    • ቀሪውን ማንኛውንም ሂሳብ ይክፈሉ።
      • ከየሎው ካብ (Yellow Cab) ጋር ለመሳፈር፣ ይህ በጥሬ ገንዘብ ወይም በክሬዲት/ዴቢት ካርድ ሊከናወን ይችላል።
      • በሊፍት (Lyft) ወይም ኡበር (Uber) መሳፈሪያዎች ላይ ቀሪ ሂሳቦችን በስማርትፎን /የእጅ ስልክ ውስጥ ባለው መተግበሪያ ፋይል ላይ በመጠቀም ክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ መከፈል አለባቸው።
  • እባክዎ ለአሽከርካሪዎ ጉርሻ መስጠትን ያስታውሱ!
    • ለየሎው ካብ (Yellow Cab): በወረቀት ቫውቸር ላይ ያለውን ቀሪ ሂሳብ ለጉርሻ መጠቀም ይቻላል፣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ጉርሻ መስጠት ይችላሉ።
    • ለሊፍት (Lyft) ወይም ኡበር (Uber): ሾፌሮችን በስማርትፎን/ የእጅ ስልክ መተግበሪያ ውስጥ በፋይል ላይ ያለውን የክሬዲት ወይም የዴቢት ካርድ በመጠቀም ጉርሻ ማድረግ ይቻላል።
    • ዲጂታል የማስተዋወቂያ የምስጢር አሀዞች በሊፍት (Lyft) ወይም ኡበር (Uber) መሳፈሪያዎች ላይ ለጉርሻ መጠቀም አይቻልም።

ደረጃ 4፡ ግብረ መልስ ይስጡ (ይበረታታል)

  • የወደፊት አገልግሎቶችን መልክ ለማስያዝ የሚረዳ ስለተሳፈሩባቸው አስተያየት ለመስጠት የሚችሉበት እና ግብአት አጭር የዳሰሳ ጥናት ይደርስዎታል።

እንደ ቀላል ይሰማል! በአሁኑ ጊዜ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ሌሎች ተደራሽ፣ በዋጋ ተመጣጣኝ የመጓጓዣ ፕሮግራሞች አሉ?

አዎ። የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ አጠቃላይ ተደራሽ የአውቶቡስ አገልግሎት እና የመዳረሻ ትራንስፖርትን የሚያካትቱ በርካታ ተደራሽ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ፕሮግራሞችን ይሰጣል። የሕዝብ ማመላለሻ ማለፊያዎችን በቅናሽ ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች የሚያሰጥ፣ ተሳፋሪዎች የክልል የተቀነሰ ዋጋ ፈቃድ (RRFP) ካርዶችን ሊጠይቁ ይችላሉ።

በአካባቢው ያሉ ሌሎች “እንደተፈለገ በጥያቄ” የመጓጓዣ አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • በሕዝብ ማመላለሻ በኩል፣ በኦቴሎ፣ ሬኒየር ቢች፣ ስካይዌይ፣ ሬንተን እና ተክዊላ ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦችን የሚያገለግል፣ በፍላጎት ወደ ቁልፍ የሕዝብ ማመላለሻ እና የማህበረሰብ ማእከላት፣ ወይም ለተደራሽነት ብቁ ተሳፋሪዎች ከነጥብ-ወደ-ነጥብ ጉዞዎችን ያቀርባል።
  • ሃይድ ሻትልስ (Hyde Shuttles)፣ ለሽማግሌዎች እና ለአካል ጉዳተኛ ሰዎች ሰፈር-ተኮር ነጻ የሆኑ፣ ማመላለሻዎች።

የሚቀጥለውን ጉዞዎን ለማቀድ አጠቃላይ የሕዝብ ማመላለሻ መረጃን እና ግብዓቶችን ለማግኘት እባክዎን የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የመስመር ላይ የጉዞ እቅድ አውጪ መሳሪያንየሳውንድ ትራንዚት ድህረ-ገጽን ወይም የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)ን የሕዝብ ማመላለሻ ፕሮግራም ድህረ ገጽን ይጎብኙ


የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)የራይድ ናዎ (Ride Now) የሙከራ ፕሮግራም ለማዘጋጀት እና ለማስጀመር ከማን ጋር ሰራ?

የተከፈለ የካሳ ክፍያ፣ ማህበረሰብ አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ: ይህ ኮሚቴ 7 የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ሲሆን፣ ሁሉም በፕሮግራሙ መስፈርት መሰረት ብቁ ተሳፋሪዎች እና ስለ ተደራሽነት፣ የመንቀሳቀስ ፍላጎት፣ የቋንቋ ተደራሽነት ምርጥ ተሞክሮዎችን እና ሂደታችንን ማሻሻል የረዱ ሌሎች የማህበረሰብ አመለካከቶችን ያካተቱ በርካታ እውቀቶችን ያመጣል።

ሌሎች ቡድኖች አብረናቸው አጋርነት የፈጠርናቸው የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • ትራንዚት ፕላኒንግ 4 ኦል (Transit Planning 4 All): Transit Planning 4 All የአካታች እቅድ አሰራርን ለመቃኘት እና ለማስተዋወቅ የሚፈልግ እና የአካል ጉዳተኞችን እና አዛውንቶችን ጨምሮ በማመላለሻ እቅድ ውስጥ የተሻሉ ልምዶችን ለማዳበር እና ለማሰራጨት የሚፈልግ ብሔራዊ የማመላለሻ-እቅድ እቅድ ነው። ትራንዚት ፕላኒንግ ለሁሉም (Transit Planning 4 All) ይህንን የሙከራ መርሃ ግብር ተግባራዊ ለማድረግ የእርዳታ ፈንድ ሰጡ።
  • የድምጽ ትውልዶችሌክ ሲቲ/ኖርዝጌት የአዛውንት ማእከል ፕሮጀክት: የሌክ ሲቲ-ኖርዝጌት የአዛውንት ማእከል ፕሮጀክት ፍትሃዊነት እና ማካተት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ‘ያለ ግድግዳ’ አካሄድ ይወስዳል። በሁሉም አስተዳደግ ውስጥ ያሉ አዛውንቶች እንደ ላቲን ዳንስ፣ ማህጆንግ፣ የስነጥበብ መማሪያ ክፍሎች፣ የባህላዊ በዓላት፣ ነጻ/ልገሳ-ተኮር ገበታዎች እና ሌሎችም ባሉ ፕሮግራሞች እና ተግባራት ይሳተፋሉ። ማዕከሉ በቀጥታ በማህበራዊ ስራ ግንኙነቶች፣ በግልጋሎት መድረስ፣ በግብአቶች፣ እና ደንበኞችን እቤት በመጎብኘት እንዲሁም በሰሜን ምስራቅ ሲያትል ያሉ አዛውንቶችን በተለያዩ ፍላጎቶች ለድጋፍ ምሪቶችን በማድረግ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
  • የኪንግ ካውንቲ ሜትሮየፈጠራ እንቅስቃሴ ፕሮግራም: የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ፈጠራ እንቅስቃሴ ፕሮግራም አዳዲስ የተንቀሳቃሽነት አገልግሎቶችን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሰዎች በኪንግ ካውንቲ በበለጡ መንገዶች እንዲዘዋወሩ ያደርጋል። በስልታዊ የምርምር ተነሳሽነቶች እና በሙከራ አገልግሎቶች፣ ሜትሮ (Metro) እንደ የጋራ ተንቀሳቃሽነት፣ ተንቀሳቃሽነት-እንደ-አገልግሎት፣ በራስ-ሠር ተሽከርካሪዎች እና ስማርት ከተሞች ያሉ አዳዲስ የመጓጓዣ ዘዴዎችን እየፈለገ ነው። ሜትሮ (Metro) ምርጦቹ ፈጠራዎች የሚመጡት በመንግስት ወኪሎች፣ ማህበረሰቦች እና የግሉ ክፍል መካከል ካለው አጋርነት እንደሆነ ያምናል።

በማጠቃለል

ብቁ የሆኑ የማህበረሰብ አባላት በመጋቢት፣ ሚያዝያ እና ግንቦት 2022 በራይድ ናዎ (Ride Now) የሙከራ ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ ተስፋ እናደርጋለን።

የበለጠ ለማወቅ እባኮትን www.seattle.gov/transportation/RideNow ይጎብኙ እና ቫውቸሮችዎን ዛሬ ይጠይቁ!

አዛውንት የሲያትል ማህበረሰብ አባላት በሊንክ (Link) ቀላል ባቡር ለመሳፈር ሲዘጋጁ የሚያሳይ ፎቶ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
አዛውንት የሲያትል ማህበረሰብ አባላት በሊንክ (Link) ቀላል ባቡር ለመሳፈር ሲዘጋጁ የሚያሳይ ፎቶ። የፎቶ ዕውቅናው: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

Ride Now ፕሮግራም ዓላማ እና ጥቅማ ጥቅሞችን እንደገና ማጠቃለል:

  • Ride Now ፕሮግራም ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች እና ተንከባካቢዎቻቸው ፈጣን፣ ቀላል እና በዋጋ ተመጣጣኝ ተደራሽነት ለማቅረብ የታሰበ ነው።
  • ግልቢያዎቹ የእንቅስቃሴ አማራጮችን ለመጨመር እና ሰዎች በአቅራቢያቸው ወዳለው የሕዝብ ማመላለሻ ቦታ ላይ እንዲደርሱ ለመርዳት የታለመ ነው – በአቅራቢያው ያለ ሊንክ (Link) የቀላል ባቡር ጣቢያ ወይም የክልል አውቶቡስ ማቆሚያ – ወይም ሌላ አጭር የአከባቢ ጉዞ ወደ ፍላጎት መድረሻ የእነዚህን የማህበረሰብ አባላት የዕለት ተዕለት የኑሮ ጥራትን ለማሻሻል ይረዳል።
  • ይህ በተለይ ያለው የሕዝብ ማመላለሻ አማራጮች ወደ አንድ ሰው ቤት ወይም እንደ የአካባቢ መናፈሻ ወይም የቤተሰብ አባል ቤት ያሉ ሌላ በአቅራቢያ ያሉ መድረሻዎች ድረስ መራዘም እስካልሆኑ ድረስ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
  • ይህ የሙከራ መርሃ ግብር የሕዝብ ማመላለሻ መዳረሻ እንቅፋቶችን ለመቀነስ እና የአዛውንቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ወይም ሌሎች የመንቀሳቀስ ፍላጎቶችን ክፍተት ለማስተካከል ይረዳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

የበለጠ ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የመጓጓዣ አማራጮችን ለሁሉም ለማቅረብ፣ በዕድሜ የገፉ የማህበረሰብ አባላትን፣ አካል ጉዳተኞችን ወይም የተለየ የመንቀሳቀስ ፍላጎት ያላቸውን፣ ተንከባካቢዎቻቸውን እና ሁሉንም የሲያትል ነዋሪዎችን ለማገልገል በመቀጠል ወደፊት እናመትራለን!