Please note: you can return to the English version of this blog post by clicking here.
ማጠቃለያ:
- በመኸር ወቅት፣ ሁላችንም የምንኖርበትን ቦታ ወይም አንድ የንግድ ድርጅት ባለቤት የሆንበት አካባቢ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመትከያ ቁራጭ መሬቶችን እና የውሃ ፍሳሽ ቦዮችን ለማጽዳት የየድርሻችንን መወጣት ይፈለግብናል።
- ይህ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የእግረኛ መንገዶችን ከወደቁ ቅጠሎች እና ልቀው ካደጉ እፅዋት አጽድቶ ማቆየት ለሁሉም ሰው መዘዋወርን ቀላል ያደርገዋል እና የእግረኛ መንገዱ ሲረጥብ ወይም ከቅዝቃዜ የተነሳ የመንሸራትት አደጋዎችን ይቀንሳል።
- ይህ የብሎግ ልጥፍ በከተማ ውስጥ በእግር የሚሄዱ እና የሚያንከባለሉ ሰዎችን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ መዳረሻን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚችሉ መርዳት ላይ አስታዋሾችን እና ጥቆማዎችን ያካትታል።
ቅጠሎችን ማስወገድ በተለይም የተደራሽነት ፍላጎት ላላቸው ወይም ለመዘዋወር ለሚቸገሩ ሰዎች፣ የእግረኛ መንገዱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሁሉም ሰው እንዲጓዝበት ሆኖ እንዲቆይ ያደርገዋል። ትክክለኛነቱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን – ደግሞም ህጉ ነው። በእርስዎ ከመንገድ ዳርቻ እና ከንብረትዎ መስመር መካከል ያለው ቦታ፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የመትከያ ቁራጭ መሬት አካባቢዎች ላይ ያሉ ቦታዎችን እና እፅዋትን ጨምሮ ተንከባክቦ የመጠበቅ እና በጥሩ ጥገና የመጠበቅ ሃላፊነት የእርስዎ ነው።
በተጎራባቾችዎ ውስጥ ያሉ ሰዎች በእግር ሲሄዱ፣ ሲያንከባልሉ፣ ብስክሌት ሲጋልቡ ወይም ሲነዱ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ምን ማድረግ እንደሚችሉ አንዳንድ የተለዩ ጥቆማዎች እዚህ አሉ። እባክዎን እነዚህን ነገሮች ማድረግ ካልቻሉ፣ እንዲረዳዎት አንድ ሰው መጠየቅን ያስቡበት።
- ከንብረትዎ ቀጥሎ ያሉ እፅዋትን ቢያንስ ቢያንስ እስከ 8 ጫማ ከእግረኛ መንገድ በላይ እና ከመንገዱ 14 ጫማ ከፍ ያድርጉት። (ስለ ዛፍ መከርከም በተጨማሪ ያንብቡ)።
- በእግረኛ መንገዱ ማንኛውንም ክፍል የሚንጠለጠል እፅዋትን ወደ ኋላ ይከርክሙ።
- የወደቁ ቅጠሎችን ከእግረኛው መንገድ ያስወግዱ።
- ከእግረኛው መንገድ ላይ የምሬት/ የድንጋይ ሽበት/ ሻጋታ እና ፍርስራሾችን ያስወግዱ።
የተዘጉ የውሃ ፍሳሽ ቦዮችን መጥረግ አይርሱ! አንድ የውሃ መውረጃ ቱቦ ከታገደ እና የዝናብ ውሃ በአግባቡ ማፍሰስ ካልቻለ፣ ሰዎች በእግር ለመሄድ እና ለማንከባለል የሚጠቀሙበት አካባቢ፣ በተለይም መንገድ ጥግ መወጣጫዎች ግርጌ ላይ በጐርፍ ሊጥለቀለቅ ይችላል። ይህ የእጅ ተሽከርካሪ ወንበሮችን ለሚጠቀሙ ሰዎች የመንገድ ጥግ መወጣጫውን አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ያደርገዋል። ያስታውሱ፣ ቅጠሎችን በሚያጸዱበት ጊዜ፣ እባክዎትን እነርሱ ወደ ውሃ መውረጃው ውስጥ እንደማይገቡ ያረጋግጡ። ቅጠሎችን በአረንጓዴ ምግብዎ እና በግቢዎ የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ውስጥ ቢተው እጅግ ይበጃል።
ሰፈርዎን በእግር ለሚሄዱ እና ለሚያንከባልሉ ሰዎች ደኅንነት የተጠበቀ ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ ከጎረቤቶችዎ ጋር ስለ ምን ማድረግ እንደምትችሉ አብረው እንዲነጋገሩ እናበረታታዎታለን። የእግረኛ መንገዶቻቸውን እና በአቅራቢያቸው ያሉትን የመንገድ ዳር መወጣጫዎች ማጽዳት፣ ዛፎችን መከርከም ወይም በሕዝብ ቦታዎች እፅዋቶቻቸውን መንከባከብ የማይችሉ ጎረቤቶቻችሁን በአካል መርዳት ከቻሉ – እባክዎትን በየጊዜው ማየት እና እርዳታ መስጠትን ያስቡበት።
ስለ የእግረኛ መንገድ ደህንነት፣ ስለዛፍ መከርከም፣ ስለ ዛፍ እንክብካቤ እና ተጨማሪ ይወቁ:
- ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት፣ የደንበኛ አገልግሎት መስመራችንን በ 206-684-ROAD (206-684-7623) በመደወል ወይም በኢሜይል 684-road@seattle.gov ያግኙ። የትርጉም አገልግሎቶች በነፃ ይገኛሉ!
- ስለ ዛፍ መከርከም ያንብቡ።
- የእርስዎን ግምታዊ የንብረት መስመር ያጣሩ።
- ስለ የእግረኛ መንገድ ጥገና፣ የባለቤቶች እና የነዋሪዎች ግዴታዎች፣ እና በረዶ እና በረዶን ስለማስወገድ ህጎችን ይማሩ።
ምንም እንኳን ክረምቱ ገና እዚህ ባይሆንም፣ ሁሉም ሰው ክረምቱ ከመድረሱ በፊት አሁን ለበረዶ እና ለበረዷማ የክረምት የአየር ሁኔታዎች መዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
ዓመቱን በሙሉ ለክረምት የአየር ሁኔታ እንዘጋጃለን። መንገዱ ከወደቁ ዛፎች እና ቅርንጫፎች እስከ በረዶ እና የበረዶ አንኳር ድረስ ሁሉንም ነገር እየጸዱ ሆነው እንዲቆዩ፣ የመንገድ ላይ ጉድጓዶችን ለመጠገን ጎዳናዎች የተስተካከሉ እንዲሆኑ እና በከተማው ሁሉ ውስጥ ምልክቶችን እና መብራቶችን ተጠግነው እንዲቆዩ እንሰራለን። እንዲሁም ሁኔታዎችን በቅርብ እንከታተላለን እና ሰራተኞቻችን ከፍተኛ አውሎ ንፋስ፣ ከባድ ዶፍ ዝናብ፣ ወይም በረዶ እና የበረዶ ጠጠር ሲሆኑ ወደ ስራ ለመሄድ ዝግጁ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
እኛ እየተዘጋጀን ነው፣ እና እርስዎም እንዲሁ ማድረግ አለብዎት! ለመዘጋጀት ምን ማድረግ የሚችሉት ይኸው፣ እና አውሎ ነፋሱ ከመምታቱ በፊት ከጨዋታው ቀደመው ይገኙ:
- ከሲያትል የበረዶ መስመሮች ጋር ይተዋወቁ። እርስዎ ወደሚፈልጉበት ቦታ ለመድረስ ከሁሉ ልቆ አስተማማኝ መንገድ እንዲሆኑ፣ እነዚህ መንገዶች ለመጥረግ ቅድሚያ የምንሰጣቸው መንገዶች ይሆናሉ። አንዴ በረዶ ከጣለ፣ የትኞቹን መንገዶች እንደጠረግን እና የአሁን የመንገድ ሁኔታዎችን በእውነተኛ ተጨባጭ ጊዜ ማሻሻያዎችን የቀጥታ የካሜራ መጋቢዎችን ለማየት ይህንን የመስመር ላይ የክረምት የአየር ሁኔታ ምላሽ ካርታ ይጠቀሙ።
- በማዕበል ጊዜ የመንቀሳቀስ እርዳታ የሚያስፈልገው ማን እንደሆነ ለማየት ጎረቤቶችዎን ያነጋግሩ እና በብሎክ ላይ ያሉት ሁሉም የእግረኛ መንገዶች አካፋ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እቅድ ያውጡ። የመኪና መግቢያ መንገድዎን እና የእግረኛ መንገድዎን ለማፅዳት እገዛ ከፈለጉ፣ ለእርዳታ ማንን መጠየቅ እንደሚችሉ ያስቡበት።
- ከፍተኛ የግዥ ፍላጎት ውስጥ ከመሆናቸው በፊት ሙቅ ልብሶችን፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶችን እና የእጅ ባትሪዎችን ያከማቹ።
- በረዶን እና የበረዶ ድንጋዮችን ለመጥረግ የበረዶ አካፋ እና የመንገድ ጨው ከረጢት ያግኙ።
- የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ጥቅሎች እና የሶስት ቀን የምግብ፣ የውሃ እና የመድሃኒት አቅርቦት እንዳለዎት ያረጋግጡ።
ስለ ክረምት የአየር ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት seattle.gov/transportation/winterweather ን ይጎብኙ። የከተማውን አጠቃላይ የክረምት አውሎ ነፋስ/ ዝናብ ምላሽ በተመለከተ ተጨማሪ ምንጮች ደግሞ seattle.gov/winterweather ላይ ይገኛሉ።
ስላሳዩ ፍላጎት እናመሰግናለን፣ እና እዚህ SDOT ካለን ከእያንዳንዳችን ሁሉ፣ አንድ ደህና የሆነ እና አስደሳች የፀደይ እና የክረምት ወቅት እንዲሆንልዎ እንመኝልዎታለን።