Find Posts By Topic

ግንባታ በባላርድ ድልድይ/15ኛ አቬኑ ሰሜን ምዕራብ ንጣፍ፣ ደህንነት፣ እና የመንገድ ማሻሻያዎችን ተጀመረ | የቀረጥ ዶላሮች በሥራ ላይ

Please note: you can find the English version of this blog post here.

የሌሪ ዌይ ድልድይ እና የባላርድ ድልድይ የአየር ላይ እይታ ከበስተጀርባ፣ ደቡብ ምስራቅን ይመለከታል። ፎቶ ክሬዲት፥ ሉክ ጋርድነር
የሌሪ ዌይ ድልድይ እና የባላርድ ድልድይ የአየር ላይ እይታ ከበስተጀርባ፣ ደቡብ ምስራቅን ይመለከታል። ፎቶ ክሬዲት፥ ሉክ ጋርድነር

የብሎግ ስታትስቲክስ፥ 1,200 ቃላት | የ6 ደቂቃ ንባብ

በጨረፍታ፥

 • ግንባታ በ 15ኛው ኣቨኑ ምዕራብ/ሰሜን ምዕራብ እና በባላርድ ብሪጅ ማንጠፍ፣ እና የደህንነት ፕሮጀክት የሚጀምረው ከሃምሌ 8 ጀምሮ ነው።
 • በባላርድ እና በኢንተርባይ መካከል ያለውን 15ኛ አቨኑ W/NW እያሻሻልን ነው። ይህም መንገድ ላይ ማንጠፍን፣ ለአውቶቡሶች ቀለል ያለ ጉዞ ማድረግን፣ እና አዲስ የትራፊክ ምልክት እና ሌሎች ባህሪያትን በመጨመር የእግር ጉዞን፣ ብስክሌት መንዳትን፣ እና መንከባለልን ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግን ይጨምራል።
 • ይህ የብሎግ ልጥፍ ከዚህ ክረምት (summer) ጀምሮ በግንባታ ወቅት ምን እንደሚጠብቁ ይነግርዎታል።
 • ፕሮጀክቱ በባላርድ ድልድይ ላይ አስፈላጊ የጥገና ሥራን ያካትታል። በድልድዩ ላይ ጥገና እና ንጣፍን ለመጨረስ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚወስደውን ጎዳና ሌሊት ሌሊት መዝጋትን እና የመንገድ ቅነሳዎችን ማከናወን አለብን። እነዚህ ከሃምሌ 8 ጀምሮ በተወሰኑ የሳምንት ምሽቶች ላይ ይከናወናሉ።
 • እንዲሁም ያረጁ የድልድይ ክፍሎችን ለመተካት እና ሌሎች ስራዎችን ለማጠናቀቅ በበልግ ወራት (fall) መጀመሪያ ላይ ድልድዩን መዝጋት አለብን። የመንገዶችን ለውጥ እና ሙሉ በሙሉ ድልድይ በሚዘጋበት ጊዜ እንዴት መዞር እንደሚችሉ ለበለጠ መረጃ ይከታተሉ።
 • ለአዳዲስ ዝመናዎች፣ የእኛን ድረ-ገጽ ይጎብኙ እንዲሁም ለኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ

ግንባታው በ15ኛ መንገድ ምዕራብ/ሰሜን ምዕራብ በባላርድ እና ኢንተርባይ መካከል ይጀመራል፣ ስራውም ሀምሌ 8 አካባቢ ይጀምራል።

ይህ ፕሮጀክት ደህንነትን እና ተንቀሳቃሽነትን ያሻሽላል። የ107 አመት እድሜ ያለው የባለርድን ድልድይ ጨምሮ የፕሮጀክቱን አካባቢ ለመጠገን እና ለማዘመን አስፈላጊ የሆኑ ስራዎችን እየሰራን ነው፣ ይህም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚቆይ ለማረጋገጥ ነው። ሌላው ግብ 15th ኣቨኑ ሰሜን ምእራብ (NW) ለእግር ጉዞ፣ ለቢስክሌት ግልቢያ፣ እና ለሚንከባለሉ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተወዳጅ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ሊጠብቁዋቸው የሚችሏቸው አንዳንድ ማሻሻያዎች እነሆ፡-

 • እንደገና የተነጠፈ ጎዳናዎች
 • የድልድይ ጥገና እና ሌሎች ጥገናዎች
 • አዳዲስ ምልክቶች እና የእግረኛ ማቋረጫዎች
 • የመጓጓዣ ማሻሻያዎች
 • የመሬት ገጽታ ያላቸው የመንገድ ማከፋፈያዎች
 • አዲስ ስንክልና ላለባቸው (ADA)-ተደራሽ ከርብ መወጣጫዎች
 • የተሻለ መብራት

ይህ ፕሮጀክት በመራጭ በተፈቀደው ሲያትልን ለማንቀሳቀስ ሌቪ የተደገፈ ነው።

የፕሮጀክት የጊዜ ሰሌዳ

 • ከሀምሌ 8 ጀምሮ ሥራ እንጀምራለን
 • ግንባታው በ2024 ይከናወናል እና እስከ 2025 ድረስ ይቀጥላል።
 • በዚህ ክረምት (summer) እና መኸር (fall) መጀመሪያ ላይ የታቀዱ ተከታታይ የድልድይ መዘጋቶች ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል።

በግንባታው ወቅት ምን እንደሚጠበቅ

በአጠቃላይ፣ እርስዎ የሚጠብቁት ነገር ይኸውና፡-

 • አንዳንድ መንገዶችን እና ጎዳናዎችን ለአሽከርካሪዎች በጊዝያዊነት እንዘጋለን።
 • ለተሽከርካሪዎች እና ለአውቶቢሶች ጊዜያዊ ማዞሪያዎች ይኖሩናል።
 • አንዳንድ የእግረኛ መንገዶችን እና መሻገሪያዎችን ለጊዜው እንዘጋለን እንዲሁም የመንገድ ለውጥ እናደርጋን።
 • አንዳንድ የአውቶቡስ ማቆሚያዎችን ለጊዜው ቦታ እንቀይራለን።
 • በመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ለጊዜው ቦታ እንቀይራለን።
 • በስራ ሰዓታት ጩኸት ይሰማዎታል፣ አቧራ ይመለከታሉ፣ እና ንዝረት ይሰማዎታል።
 • ከስራ ቦታዎች አጠገብ ለግንባታ መስሪያ የመያስፈልጉ ዕቃዎች ሊከመሩ እና የመኪና ማቆሚያ ተጽእኖዎች ይኖሩናል።
 • አልፎ አልፎ የምሽት እና የሳምንት መጨረሻ ስራዎችን መስራት አለብን።

የባላርድ ድልድይን ለአንድ ሌሊት ወደ ደቡብ አቅጣጫ መዘጋት (ከሀምሌ 8 ጀምሮ)

 • በባላርድ ድልድይ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚሄዱ መንገዶችን በጊዝያዊነት ሌሊቱን እንዘጋለን (ዘወትር ሰኞ እስከ ዘወትር ሀሙስ ከሌሊቱ 10 ሰአት በኋላ) እንዲሁም የሰሜን አቅጣጫ ጉዞን ለአንድ ሌሊት ወደ አንድ መስመር በመቀነስ በባላርድ ድልድይ ላይ ያለውን የድልድይ ጥገና እና የንጣፍ ስራን በዚህ ክረምት (summer) ከሀምሌ 8 ጀምሮ ማጠናቀቅ።
 • ባለርድ ድልድይ በእያንዳንዱ አቅጣጫ 2 መስመሮች አሉት። በእያንዳንዱ አቅጣጫ የመስመር/መንገድ ቅነሳ ከምሽቱ 7 ሰዓት ጀምሮ ሊጀምር ይችላል፣ እንዲሁም ሁሉንም ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚሄዱትን መስመሮች ከሌሊቱ 10 ሰዓት እስከ ጧቱ 5 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ በግምት ከ6 እስከ 8 ሳምንታት ያህል እንዘጋለን ብለን እንጠብቃለን።
 • የማዞሪያ መንገዶች አሁንም በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፣ ነገር ግን ወደ አውሮራ ኣቨኑ ኖርዝ (SR 99) የሚነዱ ሰዎችን አቅጣጫ እንዲቀይሩ እንጠብቃለን። እንዲሁም የፍሪሞንት ድልድይ፣ ምንም እንኳን የአቅም ውስንነት ቢኖረውም ኣለ።
 • በባላርድ ድልድይ አንድ ጎን መተላለፊያ ላይ በእግር ለሚጓዙ እና ብስክሌት ለሚነዱ ሰዎች ክፍት እንዲሆን እንጠብቃለን፣ ምንም እንኳን ስራ በሚከናወንበት ጊዜ የመዳረሻ ቦታዎች ሊለዋወጡ ቢችሉም። እባክዎትን በስራው ዞን ዙሪያ የተለጠፉትን መመሪያዎችን እና የማዞሪያ ምልክቶችን ይከተሉ።
 • የቅርብ ጊዜ ዝመናዎችን ለማግኘት፣ በፕሮጀክታችን የኢሜል ዝመናዎች መመዝገብ ይችላሉ። እንዲሁም ትራንዚት ተሳፋሪዎች የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የአገልግሎት ምክሮችን እንዲከተሉ እናበረታታለን እንዲሁም ለመጓጓዣ ማንቂያዎች ይመዝገቡ መረጃን ለማግኘት

የባላርድ ድልድይ ሙሉ ቅዳሜና እሁድ መዘጋት (ሴፕቴምበር/ጥቅምት 2024)

እንዲሁም የ107 አመት እድሜ ያለው ድልድይ በጥሩ የስራ ሁኔታ ላይ እንዲቆይ ለማድረግ በበልግ መጀመሪያ ላይ በተመረጡ ቅዳሜዎች እና እሁዶች የባላርድ ድልድይ ሙሉ በሙሉ ለጥገና መዝጋት አለብን።

የሳምንት መጨረሻ ላይ የመዝጊያ ቀናት (ወደፊት የሚረጋገጡ እና ሊለወጡ የሚችሉ)

 • ዓርብ ምሽት፣ መስከረም 6፣ 2024፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ መስከረም 9፣ 2024
 • ዓርብ ምሽት፣ መስከረም 13፣ 2024፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ መስከረም 16፣ 2024
 • ዓርብ ምሽት፣ መስከረም 27፣ 2024፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ መስከረም 30፣ 2024
 • ዓርብ ምሽት፣ ጥቅምት 4፣ 2024፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ ጥቅምት 7፣ 2024
 • ዓርብ ምሽት፣ ጥቅምት 11፣ 2024፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ ጥቅምት 14፣ 2024

እነዚህ መዘጋቶች የማይመቹ ሊሆኑ እንደሚችሉ እናውቃለን። አስተማማኝ ካልሆነ በስተቀር ድልድዩ ለሚራመዱ፣ ሮል ለሚያደርጉ፣ እና ቢስክሌት ለሚነዱት ክፍት እንዲሆን የተቻለንን እናደርጋለን። ስለ ተዘዋዋሪ መንገዶች እና በእነዚህ መዘጋት ጊዜ እንዴት መሄድ እንዳለብን ለወደፊት ዝማኔ እናጋራለን።

የግንባታው የጊዜ ሰሌዳ እንደ አየሩ ሁኔታ፣ የቁሳቁስ አቅርቦት፣ እና ሌሎች ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ሁልጊዜ ሊለዋወጥ ይችላል። ይህንን ልጥፍ ከጎረቤቶችዎ፣ ከስራ ባልደረቦችዎ፣ ከቤተሰብዎ አባላት፣ እና በ15ኛው Ave W/NW ኮሪደር አጠገብ ለሚኖሩ፣ ለሚሰሩ፣ እና ለሚጫወቱ ጓደኞችዎ እንዲያካፍሉ እናበረታታዎታለን። እንዲሁም መረጃን ለማግኘት በኢሜይል ዝመናዎች መመዝገብ ይችላሉ።  

ቀጥሎ ፕሮጀክቱ የሚገነባው እና የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እነሆ፡-

የፕሮጀክቱ ዋና ባህሪያት

 • 15 አቬኑ W/NW ከW Emerson St እስከ NW 57th St፣ የባላርድ ብሪጅን ጨምሮ (ተንቀሳቃሹን ክፍል ሳይጨምር) ንጣፍ ማልበስ፣ ይኸውም ለአውቶቡስ ተሳፋሪዎች፣ ለጭነት፣ እና ለአሽከርካሪዎች ምቹ ጉዞ ለማድረግ።
 • 107 አመት እድሜ ባለው የባለርድ ድልድይ ላይ ጥገና ማድረግ፣ ድልድዩ ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ እና ያረጁ የማስፋፊያ መገጣጠሚያዎችን መተካት እና እንቅስቃሴን፣ የሙቀት ለውጦች፣ እና ከፍተኛ የአየር ሁኔታዎችን መቋቋም መቻልን ይጨምራል።
 • በከፍተኛ የመጓጓዣ ሰአታት ጊዜ የ RapidRide D የአውቶቡስ ጉዞዎችን ለማፋጠን አዲስ ቀይየአውቶቡስ ብቻመስመሮች በ 15th Ave NW ክፍሎች ማለት በ NW Market St እና Leary Way Bridge መካከል።
 • አዲስ የብስክሌት እና የእግረኛ ምልክት እና የእግረኛ ማቋረጫ NW 51st St ወደ ባላርድ ንግዶች፣ መስህቦች፣ እና የአውቶቡስ ማቆሚያዎች የሚሄዱ፣ የሚንከባለሉ፣ እና ቢስክሌት የሚነዱ ሰዎች ተደራሽነትን እና ደህንነትን ለማሻሻል።
 • የትራፊክ ፍጥነትን ለማረጋጋት እና የጉዞ ደህንነትን ለማሻሻል በ15th Ave NW በ NW 50th St እና NW 54th St መካከል አዲስ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው ሚዲያን
 • የአካለ ስንኩላን (ADA) ተደራሽነት ደረጃዎችን የሚያሟሉ የእግረኛ መንገድ ማሻሻያዎች እና የከርብ ራምፕስ መተካት

ሁሉንም የፕሮጀክት ዝርዝሮች እና በ15th Ave W/NW የታቀዱ ማሻሻያዎችን ለማየት ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ

እንዲሁም (ከባላርድ ድልድይ በስተሰሜን) ያለው የሌሪ ዌይ ድልድይን እናጠናክራለን ይህም በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ ደህንነቱ የተጠበቀ ያደርገዋል።

የተሻሻለው ጎዳና በ15th Ave NW እና NW 51st St የፕሮጀክት ስራ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
የተሻሻለው ጎዳና በ15th Ave NW እና NW 51st St የፕሮጀክት ስራ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ገጽታ። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

የፕሮጀክት ካርታ 

የፕሮጀክቱ አካባቢ ካርታ እና ቁልፍ ማሻሻያዎች። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
የፕሮጀክቱ አካባቢ ካርታ እና ቁልፍ ማሻሻያዎች። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል ማመላለሻ መምሪያ (SDOT) 

መረጃ ለማግኘት፡

በአካባቢው ያሉ ሌሎች ፕሮጀክቶች

 በግንባታ ወቅት የጉዞ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ በአቅራቢያ ካሉ ሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር እየሰራን ነው።

ስለ እያንዳንዱ ፕሮጀክት የበለጠ ለማወቅ፣ ከዚህ በታች ያሉትን ማገናኛዎች ይጠቀሙ፡

ኮል- አውት ቦክስ፡-

የፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ

ይህ ስራ በድምጽ ሰጪዎች በተፈቀደው የገንዘብ ድጋፍ Levy to Move Seattleየተደረገ ሆኖ እንዲሁም በድምጽ ሰጪዎች ከተፈቀደው የሲያትል ትራንዚት ሜዠር የገንዘብ ድጋፍን ያካትታል። በመርከብ ቦይ (Ship Cana) በሁለቱም በኩል ንቁ የሆኑ ሰፈሮችን እና የንግድ አውራጃዎችን የሚያገናኝ ይህን ሥራ የሚበዛበት አካባቢ ለመጠገን እና ለማዘመን ጠቃሚ ኢንቨስትመንት ነው።

የሌሪ ዌይ ድልድይ የመሬት መንቀጥቀጥ ፕሮጀክት ከፌዴራል እርዳታ የገንዘብ ድጋፍንም ያካትታል። የፌደራል አጋሮቻችንን የባይደን አስተዳደር፣ ሴናተር ፓቲ ሙሬይ፣ ሴናተር ማሪያ ካንትዌል፣ እና የኮንግረስ ኣባል ፕራሚላ ጃያፓልን ጨምሮ ላደረጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

በግንባታ ወደ ፊት ስንሄድ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ስለ ጊዜዎትና እና ፍላጎት እናመሰግናለን።