Please note: you can return to the English version of this blog post by clicking here.
ጸደይ እዚህ ነው! ቀለል ያሉ/ ይበልጥ ብርሃን እና ሞቃታማ ቀናት ማለት ብስክሌቶችን ማምጣት እና ለመጋለብ መዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው ማለት ነው። ከአጋሮቻችን ጋር፣ በሁሉም እድሜ እና ችሎታ ያሉ ሰዎችን በከተማዋ ዙሪያ ብስክሌት እንዲነዱ ለመርዳት ብዙ ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶችን እናቀርባለን።
ብስክሌት መጋለብ፣ በእግር መሄድ እና ማንከባለል ወደ ውጭ ለመውጣት፣ ጤናማ ለመሆን እና ወደምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ ጥሩ ዘዴዮች ናቸው። እንዲሁም ብስክሌት መጋለብ በ2030 ከሁሉም የግል ጉዞዎች የከተማዋን የ90% ዜሮ ልቀት ግብ እንዲኖር ይደግፋል። ዜሮ-ልቀት የመጓጓዣ ዘዴዎች በእግር መሄድን፣ ማንከባለልን፣ ብስክሌት መጋለብን እና የሕዝብ መጓጓዣን ወይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EVs) መጠቀምን ያካትታሉ።
_____
የብስክሌት ካርታ እና መመሪያ
- የእኛ የ2022 የብስክሌት ካርታ በሲያትል ውስጥ በጣም ወቅታዊ የሲያትል የብስክሌት መስመሮችን፣ የአጎራባች አረንጓዴ መንገዶችን፣ እና ሌሎች የብስክሌት ግንኙነቶች የሆነ ካርታ ነው።
- የ2022 ካርታ በፖስታ በነጻ ተልኮ ማግኘት ይችላሉ! ቅጂ ይጠይቁ።
- ለርስዎ በሲያትል ውስጥ የቢስክሌት መንዳት የሁሉም ነገር መመሪያዎ፣ በኋላ በዚህ ወር የተሻሻለውን የሲያትል የቢስክሌት መመሪያን እናተምታለን።
ዕድሜ ለ Levy to Move Seattle አዲስ የብስክሌት መንገዶች
- በሕዝብ ምርጫ ለተፈቀደው ቀረጥ ወደ ሲያትል ማንቀሳቀስ ምስጋና ይግባውና፣ በ2021፣ ወደ 7 ማይል የሚጠጉ አዲስ የተጠበቁ የብስክሌት መስመሮችን፣ እና አዲስ የአጐራባች ግሪንዌይን ከ7 ማይል በላይ አጠናቀናል።
- ከ 2016 ጀምሮ፣ ወደ 4 ማይል የብስክሌት መስመሮችን እና 24 ማይል የተጠበቁ/ የተከለሉ (ቢስክሌት በሚጋልቡ እና በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መካከል አካላዊ መከላከያ ያለው) የብስክሌት መስመሮችን ጨርሰናል። እንዲሁም ወደ 27 ማይል የሚጠጋ የNeighborhood Greenways ፈጥረናል።
- እስኪ የሲያትል ነዋሪዎች አንዳንድ በቅርብ ጊዜ የተጠናቀቁ የብስክሌት መንገዶችን በጥሩ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሲያውሉት ለማየት ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ።
- ሲያትል፣ በቀረጥ ታክስ ዶላርዎ እነዚህን እንዲቻል ስላደረጉ እናመሰግናለን።
- መንገዶች ጤናማ ይሁኑ በእግር ለሚሄዱ፣ ብስክሌት ለሚጋለቡ እና ለሚያንከባለሉ ሰዎች ሌላው ክፍት አማራጭ ነው። እነሱ በተሽከርካሪ ትራፊክ ለማለፍ ዝግ ናቸው።
የብስክሌት ማስተካከያ/ ጥገና፣ ኪራዮች እና ብስክሌት–መጋራት
- የከተማው ብዙ የብስክሌት መደብሮች የርስዎን ብስክሌት ማስተካከል/ መጠገን እና ለመጠቀም ዝግጁ ሊያደርግልዎት ይችላሉ። የመደብሮቹን ዝርዝር እዚህ ማግኘት ይችላሉ።
- ብስክሌት የልዎትም? እንዚህን የኪራይ ወይም ከከተማው የብስክሌት መጋራት ፕሮግራሞች አንዱን ይፈትሹ።
አስቀድሞ ማቀድ
አንዴ ከተሰራ፣ ብስክሌትዎን ለመጠቀም ወደሚቀጥለው እርምጃዎች ለመሄድ ዝግጁ ነዎት። አስቀድሞ ማቀድ ደኅንነት እና ዝግጁነት እንዲሰማዎ ሊያደርግ ይችላል።
- ደኅንነትዎን እንዲጠብቅ በደንብ የሚገጥም የራስ ቁር ያግኙ።
- የት መሄድ ይሻሉ ወይም ይፈልጋሉ? በወረቀት ወይም በመስመር ላይ የ2022 የብስክሌት ካርታ በመጠቀም መስመርዎን አስቀድመው ይሞክሩ።
- የጉዞዎን እቅድ ለማውጣት የብስክሌት ተጓዦች የእገዛ ጠረጴዛን በእጆች የተግባር እገዛ ለማግኘት ይመልከቱ።
- የመንገድ ምልክቶች እና ደንቦች በአእምሮዎ ውስጥ ትኩስ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የብስክሌት መመሪያውን ይከልሱ።
- ከዚያም፣ በልምምድ ጉዞዎ ላይ አብሮዎት የሚሄድ ጓደኛዎን ይያዙ። ከሁሉም በጣም አስፈላጊው ነገር በጉዞዎ ላይ ደህንነት እና ምቾት ሲሰማዎት ነው!
ብስክሌት ሁሉም ጋ ቀንን ያክብሩ
- የብስክሌት ሁሉም ጋ ቀንን ከርስዎ የብስክሌት ጋላቢ አርቦሽዎችዎ ጋር አርብ ግንቦት 20 መቀላቀል ይችላሉ።
- በወሩ ውስጥ ሁሉ፣ ካስኬድ የቢስክሌት ክበብ ቢስክሌት ሁሉም ጋ ውድድር ያካሂዳል።
- በውድድሩ ውስጥ ያሉ ተሳፋሪዎች ጉዞዎችን መከታተል እና ማወዳደር፣ ምናባዊ ባጆችን ማሸነፍ እና ስለ ብስክሌት በመንዳት ከፍተኛ ፍቅር ካለው ማህበረሰብ መሳተፍ ይችላሉ።
- ወሩንም ሁሉ የቡድን ግልቢያዎችን በማድረግ፣ የግልቢያ የደስታ ሰዓት፣ እና ተጨማሪ የብስክሌት መቀራረቢያ ዘዴዎችን ሁሉ ለማክበር የካስኬድ ድህረ-ገጽን ይመልከቱ!
እነዚህ ከሲያትል ጉዞ የመጡ ቪዲዮዎች አንዳንድ ጎረቤቶቻችን ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ የመጓጓዣ ታሪካቸውን ሲያካፍሉ ያሳያሉ።
ይህኛው በየቀኑ ከማዕከላዊ ዲስትሪክት ወደ ትምህርት ቤት በቢስክሌት ስለሚጓዝ ስለ የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ነው:
ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ወደ ትምህርት ቤት ቢስክሌት ይጋልቡ።
- ቢስክሌት በሁሉም ቦታ ወር ወደ ትምህርት ቤት ቢስክሌት ለመንዳት እንዲሁ ጥሩ ጊዜ ነው። በግንቦት ወር፣ እንዲሁ ብሔራዊ የወደ ትምህርት ቤት የብስክሌት እና የማንከባለል ቀንን እናከብራለን።
- በዚህ ወር እስካሁን ብዙ ተማሪዎች አክብረውታል!
- በድቡብ ፓርክ ውስጥ ያለው ኮንኮርድ ዓለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን በሀብሐብ እና በነፃ ብርሃኖች፣ የቀለም ቅብ መጽሐፍት እና ባለቀለም እርሳሶች ወደ ትምህርት ቤት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለውአቸዋል። በእለቱ ብዙ ተማሪዎች በእግራቸው ወይም በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ። እንዲሁም ተማሪዎች የእግር ጉዞ እና በብስክሌት የመጡባቸውን ደቂቃዎችን በየቀኑ የሚከታተሉበት እና በወሩ መጨረሻ ሽልማቶችን የሚያገኙበትን የቀን መቁጠሪያ ወስደዋል። ኬት አይርስ (Kate Ayers) ከ 2000 ጀምሮ በኮንኮርድ እያስተማረች እና ተማሪዎችን በእግር እና በብስክሌት እንዲመላለሱ ለ22 አመታት ሁሉ ድጋፍ ስትሰጥ ቆይታለች!
- በምእራብ ሲያትል ደግሞ ያለ የጄኔሴ ሂል አንደኛ ደረጃ ወደ ትምህርት ቤት ቀን በእግር በመሄድ፣ በብስክሌት እና በማንከባለል አክብረዋል። ከ100 በላይ ልጆች ብስክሌት እና ስኩተር ነድተው ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ እና ብዙዎችም በእግር ተጉዘዋል። ተማሪዎች ከርዕሰ መምህር ዳን (Dunn) እና ከበጎ ፈቃደኞች ወላጆች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁሉም ሰው ነፃ አንጸባራቂዎችን፣ ተለጣፊዎችን፣ የቀለም ቅብ መጽሐፍትን እና የእርሳስ መያዣዎችን ተቀብለዋል።
- አንድ የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት በብስክሌት ይጓዛሉ! እዚህ የበለጠ ተማር።
እዚህ እኛ እና አጋሮቻችን እንዴት ወደ ትምህርት ቤት ብስክሌት መጋለብ እና ማንከባለልን የምንደግፍበት ሌሎች መንገዶች አሉ:
- የSDOT የወደት/ቤት አስተማማኝ መንገዶች ፕሮጀክቶች ወደ ትምህርት ቤት ደህንነቱ የተጠበቀ የእግር ጉዞ፣ ማንከባለል እና ብስክሌት መንዳትን የሚያስታውቁ፣ ከፍ የተደረጉ የእግረኛ መሻገሪያ መንገዶችን፣ በማቋረጫ መንገዶች ላይ ብልጭ ድርግም የሚሉ መብራቶችን፣ የእግረኛ ማቋረጫዎችን እና ምልክቶችን ያካትታሉ።
- በትምህርት ዓመቱ ወቅት፣ የ በደህንነት በብስክሌት እና በእግር እንሂድ እና ወደ ፊት እንሂድ ፕሮግራሞች በትምህርት አመቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ የአንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የብስክሌት እና የእግር ጉዞ ደህንነት ችሎታዎችን ያስተምራሉ። እንዲሁም እንሂድከቤት ውጭ ለሁሉም ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለአካል ጉዳተኛ ልጆች ልዩ ስልጠና ለመስጠት ይተባበራል።
- ከቤት ውጭ ለሁሉም ባለ ሶስት ወይም አራት ጎማ ዑደቶች እና የተገደበ ወይም ምንም የእግር እንቅስቃሴ የለሌላቸው የእጅ ብስከሌቶችን ጨምሮ፣ የመለማመጃ ብስክሌቶችን ያከራያል።
- የቢስክሌት ወደ ትምህርት ቤት ዝግጅቶች፣ በካስኬድ የብስክሌት ክበብ የሚስተናገዱ፣ አስደሳች ትምህርት ቤትዎን የሚያሳትፉበት ዘዴዎች ናቸው። የትምህርት ቤትዎን ክስተት ማስመዝገብዎን አይርሱ!
- የብስክሌት ባቡር ድጋፍ ቁጥጥር የሚደረግባቸው የብስክሌት ጉዞዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማደራጀት ለሚፈልጉ በካስኬድ የብስክሌት ክብብ ይሰጣል።
- ባለፈው ዓመት ተማሪዎችን በሰላም ወደ ትምህርት ቤት እንዴት እንዲጓዙ እንደረዳናቸው የበለጠ ይረዱ።
ጉዞዎን ማዞርዎን ይቀጥሉ!
- በሕዝብ መጓጓዣ ላይ፣ በውሃ ታክሲ እና በብስክሌት/ስኩተር መጋራት (የTransit GO Ticket app በመጠቀም) $25 ዶላር የሚያወጣ ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ በነጻ ጉዞዎች ጉርሻ ለማግኘት FlipYourTrip.org ላይ ይመዝገቡ።
- እንዲሁም የመጀመሪያ ወርዎን በነፃ የሜትሮ ቫንፑልስ፣ ለግል የተበጀ የጉዞ እቅድ፣ የመረጃ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም ማግኘት ይችላሉ።
- በ ካስኬድ የብስክሌት ክለብ የቢስክሌት ሁሉም ጋ ውድድር ውስጥ የጉዞዎን ይገልብጡ (Flip Your Trip) ተሳታፊዎችን ከተቀላቀሉ፣ ለአካባቢው ምግብ ቤቶች እና የብስክሌት ሱቆች የ$100 ዶላር የስጦታ ካርዶችን ለማሸነፍ ለሳምንታዊ ዕጣ ማውጫ ብቁ ይሆናሉ!
- የበለጠ ስለ ብስክሌት መንዳት በምዕራብ ሲያትል ድልድይ መዘጋት ወቅት በካስኬድ ድረ-ገጽ ላይ ይወቁ።
- የምእራብ ሲያትል የቢስክሌት ግንኙነቶች ከምእራብ ሲያትል በሚመጡ የመስመር ጥቆማዎች/ አስተያየቶች ሊረዳ ይችላሉ።
ይደሰቱ እና በብስክሌት ስለተመላለሱ እናመሰግናለን!