Find Posts By Topic

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ | ስለ ፍላጎቶችዎ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች መስማት እንፈልጋለን። አዲሱን የዳሰሳ ጥናታችንን ይውሰዱ፣ ወደሚመጣው ክስተት ይምጡ እና የቱ ጋ ለውጥ ማየት እንደሚፈልጉ ይንገሩን።


ማጠቃለያ

  • ይቀላቀሉን! በጋራ፣ በከተማው ውስጥ እንዴት እንደምንንቀሳቀስ እና በጎዳናዎቻችን እና በህዝባዊ ቦታዎች እንዴት እንደምንደሰትበት እንደገና እያሰብንበት ነው።
  • በመጀመሪያው ዙር የማህበረሰብ ማዳረስ ላይ ነን። እባክዎን ስለ ማመላለሻ ፍላጎቶችዎ እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች ይንገሩን!
  • በብዙ መንገዶች የሲያትል የማመላለሻ እቅድን ለማዳበር ማገዝ ትችላላችሁ። ለመሳተፍ አሁኑኑ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የመስመር ላይ የተሳትፎ ማእከልን ይጎብኙ።
  • የሲያትል አጠቃላይ የእቅድ ማሻሻያ ለመፍጠር የማህበረሰብ እቅድ እና ልማት ጽህፈት ቤት (OPCD) ደግሞ የእርስዎን እገዛ እየጠየቀ ነው። ይህ አንድ የሲያትል እቅድ ይባላል።

ይቀላቀሉን! በጋራ፣ በከተማው ዙሪያ እንዴት እንደምንንቀሳቀስ እና በመንገዶቻችን እና በህዝባዊ ቦታዎቻች እንዴት እንደምንደሰትበት እየቀረፅን ነው።

የሲያትል የማመላለሻ እቅድ (STP) ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የማመላለሻ ስርዓት ለመገንባት ያለን ቁርጠኝነታችን ነው።  የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) ሁላችንም ወደፊት እንዴት በከተማ ዙሪያ መንቀሳቀስ እንደምንፈልግ ለማጤን ለኛ እድሉ ነው።

STP ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የአካባቢውን የማመላለሻ መዋዕለ ንዋዮችን ይመራል፣ ስለዚህ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን!

በብዙ መንገዶች የሲያትል የማመላለሻ እቅድን ለማዳበር ማገዝ ትችላላችሁ!

የመጀመርያ ዙር የህብረተሰብ ማዳረስን ጀምረናል። እባክዎን ስለ መጓጓዣ ፍላጎቶችዎ እና ቅድሚያ ስለሚሰጧቸው ነገሮች ይንገሩን።

አዲሱን የዳሰሳ ጥናታችንን መውሰድ፣ ወደሚመጣው ክስተት መምጣት እና በሲያትል ውስጥ የቱ ቦታዎች ጋ ለውጥ ማየት እንደሚሹ ይንገሩን።

ለመሳተፍ አሁኑኑ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የመስመር ላይ የተሳትፎ ማእከልን ይጎብኙ።

አንድ ላይ፣ ለአሁን እና ለወደፊትም ለሁሉም የተሻለ የሚሰራ የማመላለሻ ስርዓት እንገነባለን።

ከአሁን ጀምሮ እስከ 2022 ክረምት፣ ከእርስዎ እና ማህበረሰብን መሠረት ካደረጉ አጋር ድርጅቶች ጋር አብረን እንሰራለን። የእርስዎን የመጓጓዣ ፍላጎቶች እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች ለመረዳት ተስፋ እናደርጋለን።

ማወቅ የምንፈልገው:

  • በሲያትል ስላለው የወደፊት የመጓጓዣ ሁኔታ ሲያስቡ፣ ምን ለማየት ተስፋ ያደርጋሉ? ለእርስዎ አስፈላጊ ምንድነው?
  • በሲያትል አካባቢ ሲዘዋወሩ፣ ምን ተግዳሮቶች ያጋጥሙዎታል? መዘዋወርን ቀላል የሚያደርገው ምንድን ነው?

ለእነዚህ እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ለመመለስ የሲያትል የማመላለሻ እቅድ የመስመር ላይ የተሳትፎ ማእከልን ይጎብኙ።

የእርስዎ መልሶች የሲያትል የማመላለሻ እቅድ መሰረትን ለመገንባት ይረዳሉ። በ2022 በልግ፣ የሰማነውን እና ተጨማሪ ጥያቄዎችን ይዘን እንመለሳለን። በ2023 ጸደይ፣ የእቅዱን ረቂቅ ከእርስዎ ጋር እናካፍላለን።

የማህበረሰብ እቅድ ማድረግ እና ልማት ጽህፈት ቤት (OPCD) ደግሞ በሲያትል አጠቃላይ ፕላን ማሻሻያ ላይ የእርስዎን አስተያየት እየጠየቀ ነው። ይህ አንድ የሲያትል እቅድ ይባላል።

አንድ የሲያትል እቅድ እንደ አስፈላጊ ውሳኔዎችን ይመራል:

  • መኖሪያ ቤት እና ስራዎች ባሉበት
  • የት እና እንዴት በማመላለሻ፣ በመገልገያዎች፣ በመናፈሻዎች እና በሌሎች ላይም ኢንቨስት እናደርጋለን።

ግቡ ሲያትልን የበለጠ እኩልነት የሰፈነበት፣ መኖር የሚቻልበት፣ ዘላቂ እና ጠንካራ መሠረት ያለው ማድረግ ነው።

የበለጠ ለማወቅ እና የሲያትልን የወደፊት ትልቅ ምስል ሁኔታን ለመምራት የ OPCD ን አንድ የሲያትል እቅድ ተሳትፎ ማዕከልን ይጎብኙ።


ስለ ሲያትል ተማመላለሻ እቅድ (STP) የበለጠ ይወቁ እና በመረጡት ቋንቋ ሃሳቦችዎን ያካፍሉ: