Please note: you can click here to return to the English version of this blog post.
የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) መሰንጠቅን ጠግኖ እና ወደ 60 ማይል የሚጠጋ የብረት ገመድ “የጀርባ አጥንት” በድልድዩ ስለጨመረ የበለጠ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
ሲያትል (ነሐሴ 11 ቀን 2022) – የሰራተኛ ቡድኖቹ የምዕራብ ሲያትል ድልድይ የጥገና ጥረት የመጨረሻ ደረጃዎቹ ላይ እንደገቡ፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያው (SDOT) በቅርብ ጊዜ የተከናወኑ የግንባታ ወሳኝ ደረጃዎች በታቀደው መሰረት መጠናቀቃቸውን እና ድልድዩን እሁድ፣ መስከረም 18 እንደገና እንደሚከፍቱ እንድሚጠበቅ አስታውቋል። ይህም ማጣበቂያ በመርፌ ሰርስሮ ማጠናቀቅን፣ የካርቦን ፋይበር መጠቅለልን፣ ንጣፍ ማንጠፍን፣ የደህንነት ፍተሻ መድረክን መትከል፣ እና ጠንካራ የደህንነት ሙከራን/ ፍተሻን ጨምሮ ቀሪው ስራ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቃቁ ላይ ይወሰናል። በስፖኬን መንገድ (Spokane St) ተወዛዋዥ ድልድይ (በተጨማሪም የምእራብ ሲያትል ዝቅተኛ ድልድይ በመባልም የሚታወቅ) ላይ የነበሩ ገደቦች ሁሉም በተመሳሳይ ቀን ያበቃሉ።
ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በ YouTube፣ Flicker፣ እና በSDOT ብሎግ ላይ ይገኛሉ።
የሲያትል ከንቲባ ብሩስ ሃሬል (Bruce Harrell) “ለዚህ አስቸጋሪ የመዘጋት ጊዜ ፍጻሜ መቃረብ በጣም እፎይታ ነው” ብለዋል። “ይህ የመንገድ መዘጋት ለብዙ ሰዎች፣ ንግዶች እና ማህበረሰቦች ምን ያህል የሚያም እንደነበረ እንገነዘባለን። ከመጀመሪያው ጀምሮ ደህንነታቸው የዚህ የጥገና ጥረት ዋና እምብርት እንደነበረ ነው። ድልድዩን እንደገና ስንከፍት እና ከተማችንን እንደገና ስናገናኝ፣ ድልድዩ አሁን የበለጠ ጠንካራ እና ለእያንዳንዱ ሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን በመተማመን ማህበረሰቦቻችንን እያሰባሰብን ነው።”
የድልድይ ተቆጣጣሪዎች ስንጥቆች በ40 ዓመቱ ግምብ ላይ በፍጥነት እየጨመሩ መሄዳቸውን ባገኙ ጊዜ የምዕራብ ሲያትል ድልድይ በመጋቢት 2020 ውስጥ ተዘግቷል። የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ተጨማሪ ስንጥቅ ለመከላከል እና ድልድዩ እንዲቆም ለማድረግ በ2020 የአስቸኳይ ጊዜ ጥገናን አጠናቀቀ። በ2021 እና 2022፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) የየእለቱን የትራፊክ ክብደት እና ጭንቀትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቋቋም ድልድዩን ለማጠናከር ይበልጥ ጠንካራ የሆነ የመጨረሻ ጥገና በመንደፍ እና በመገንባት ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
ሄዘር ማርክስ (Heather Marx)፣ “ይህ እጅግ ታላቅ ጥረት ስንጥቆቹን ጠግኖ እና ድልድዩን የበለጠ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አድርጎታል“ብለው ተናግረዋል። “የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) በመጀመሪያው የታሰበውን የሕይወት ዘመን እንደሚያሟላ፣ ድልድዩ ለመጪዎቹ አሥርተ ዓመታት በጥንካሬ እንደሚቆም እርግጠኛ ነው። እርግጠኝነታቸው ያልተረጋገጡትን የዚህን የሚፈታተን ፕሮጀክት ስንቃኝ የማህበረሰቡን የመቋቋም ችሎታ እናደንቃለን።”
በእያንዳንዱ የSDOT ፕሮጀክት ላይ ደህንነት የመጀመሪያው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ድልድዩን ከመጠገን በተጨማሪ፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) በመቶዎች በሚቆጠሩ የእንቅስቃሴ ዳሳሾች፣ ካሜራዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች በድልድዩ ውስጥ በማሰብ ችሎታ የተዋቀረ የክትትል ስርዓት ተክሏል። ይህ ስርዓት ስውር እንቅስቃሴዎችን ወይም ማንኛውንም ያሉትን የነባር ስንጥቆችን እድገት መለየት ይችላል። ድልድዩን 24/7 ይከታተላል እና የድልድይ ጥገናዎች ክንውኖችን ለሚቆጣጠሩ ሰራተኞች የእውነተኛ ጊዜ ዝርዝሮችን እና ማስጠንቀቂያዎችን ይሰጣል። በመጪዎቹ አመታት ውስጥ ተቆጣጣሪዎች የድልድዩን መዋቅራዊ አካላት በየጊዜው መመርመር እንዲችሉ በድልድዩ ውስጥ ቋሚ የፍተሻ መድረኮች ይገነባሉ።
እጅግ በጣም አስፈላጊው የጥገናው ጥረት አካል በድልድዩ ውስጥ አዲስ የብረት ድህረ-ውጥረት ስርዓትን ማጠናቀቅ ነበረ። የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) በመጀመሪያው የአስቸኳይ ጊዜ ጥገና 10 ማይል ያህል አዲስ የብረት ገመዶች እና በመጨረሻው ምዕራፍ ተጨማሪ ወደ 50 ማይል የሚጠጉ የብረት ገመዶችን ጨምረዋል። እያንዳንዳቸው የብረት ገመዶች መልህቅ የተደረጉ እና የተደገፉት በድልድዩ ላይ በተሰሩ ልዩ ቁራጭ የሲሚንቶ ትላልቅ ጡቦች የተሸመኑ እና ከ20 ሚሊዮን ፓውንድ ኃይል በላይ መያዝ የሚችሉ ናቸው።
አንድ ላይ በመሳብ እና በዙሪያው ያለውን ትልቁን የኮንክሪት መዋቅር በማጠናከር፣ ይህ የብረት ድህረ-ውጥረት ስርዓት የድልድዩን የጀርባ አጥንት ያንጻል። በ1980ዎቹ የተገነባው የመጀመሪያው የብረት ድህረ-ውጥረት ስርዓት ያልደረሰበትን የተንጣለሉ ቦታዎችን ጨምሮ፣ አዲሱ ስርዓት በዱዋሚሽ የውሃ ፈሰስ (Duwamish Waterway) ላይ በድልድዩ ሶስት እርከኖች ላይ ይዘልቃል።
በድልድዩ ግድግዳዎች ውስጥ እና ውጭ በተሰበረ አጥንት ላይ እንደተጠመጠመ ጀሶ የተጠናከረ የካርበን ፋይበር ምንጣፎች አውታረ መረብን ጨምሮ፣ አዲሱ የድህረ-ውጥረት ስርዓት በድልድዩ ላይ ከሚገኙ ሌሎች ጥገናዎች ጋር አብሮ ተጣምሮ ይሰራል። የሰራተኛ ቡድኖች ተጨማሪ መባባስን ወይም መበላሸትን ለመከላከል እና የተሰነጠቀውን ኮንክሪት አቅልጠው በማያያዝ በስፋት ማጣበቂያ በመርፌ መሰል ሰርስረው ስንጥቆቹ ውስጥ አስገብተዋል። እነዚህ የጥገና ስርዓቶች ድልድዩን ለብዙ አሥርተ ዓመታት ከባድ ትራፊክ መሸከም፣ የሙቀት ለውጦችን፣ እና ከባድ የበጋ እና የክረምት የአየር ሁኔታን ለመቆጣጠር አዘጋጅተዋል።
ድልድዩ ከመከፈቱ በፊት የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ድልድዩ መዋቅራዊ ጤንነት እና ለህዝብ ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙ ፍተሻዎችን ያደርጋል። ይህ ፍተሻ ትራፊክን እንዳለ በማስመሰል ከባድ መሳሪያዎችን በድልድዩ ላይ መንዳት እና መሐንዲሶች የሚሰጠውን የመዋቅሩን ምላሽ በእውነት ጊዜ እንዲከታተሉ እና ጥገናዎቹ እንደተጠበቀው እየሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥን ያካትታል።
ሌሎች ድልድዩ ከመከፈቱ በፊት የሚጠናቀቁት ስራዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- የመጨረሻ በመርፌ መሰል የሚሰገሰጉ እና የካርቦን-ፋይበር መጠቅለያን ማጠናቀቅ
- ለካርቦን-ፋይበር መጠቅለያው የፈውስ/የመጠንከር ጊዜን ማጠናቀቅ
- የሥራ መድረኮችን ማንሳት
- የጭነት ፍተሻ እና ጥገናዎቹን በጥንቃቄ መመርመር
- በድልድዩ መዋቅር ውስጥ ቋሚ የፍተሻ መድረኮችን መትከል
- በድልድዩ ወለል ላይ ያለውን ንጣፍ ወደነበረበት መመለስ
- የግንባታ መሳሪያዎችን ማንሳት እና ድልድዩ ለህዝብ የተዘጋጀ ማድረግ
በበጋው ወቅት ሁሉ ሥራው በተረጋጋ ሁኔታ እየተካሄደ እያለ፣ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የቀሩት ጥገናዎች እና ፍተሻ ማካሄድ ፈታኝ እና ውስብስብ ሥራን ይጠይቃል። የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) በመካሄድ ላይ ያሉ የግንባታ ማሻሻያዎችን ለማቅረብ ቆርጦ ተነስቷል እና ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶች የድልድዩን መክፈቻውን ቀን የሚያደናቅፍ ከሆነ ለህዝቡ ያሳውቃል።
በጥገናው ሂደት ሁሉ፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) የደቡብ መናፈሻን፣ ጆርጅታውንን፣ እና የምዕራብ ሲያትል ማህበረሰቦችን በእቅድ እና በመድረስ በኩል ግንባር እና ማዕከል አድርጓል። ከድልድይ ጥገናዎች በተጨማሪ፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) ትራፊክን ለማረጋጋት እና የድልድይ ትራፊክ በሌላ አቅጣጫ እንዲዞሩ የተደረገባቸው ማህበረሰቦች እና እንደ Highland Park እና Duwamish Valley ባሉ የንግድ ወረዳዎች ሰፈሮች ውስጥ ትራፊክን ለማረጋጋት እና የአጎራባች መንገዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር በፕሮጀክቶች ላይ አፍስሷል።
ሰዎች እየተናገሩ ያሉት ነገር:
የሲያትል ከተማ ምክር ቤት አባል ሊዛ ሄርቦልድ (Lisa Herbold) “ከተዘጋ ጊዜ ጀምሮ፣ ሁሉም ዌስት ሲያትል፣ የደቡብ ፓርክ እና ጆርጅታውን የድልድዩ እንደገና መከፈትን በአእምሮአቸው ላይ ከፍ አድርገዋል” ብለዋል። “ከቀሪው ሲያትል ጋር እኛን ለማገናኘት ድልድዩ የአጭር ጥቂት ሳምንታት ጊዜ በመቅረቱ ምክንያት እኔ ዛሬ የእፎይታ አየር እየተነፈስኩ ነው።”
የሲያትል ከተማ ምክር ቤት አባል አሌክስ ፒደርሰን (Alex Pedersen) “በመጨረሻም ለዚህ ወሳኝ ድልድይ የተወሰነ የመክፈቻ ቀን ስላለን ከምዕራብ ሲያትል እና ከቀጠናው አካባቢ ጋር እፎይታውን እጋራለሁ” ብለዋል። “ከሁለት ዓመት በላይ ከፈጀ ጥገናዎች በኋላ ይህን ድልድይ እንደገና ለመክፈት በጉጉት እየተጠባበቅኩ ሳለ፣ ይህ ተውኔታዊ መዘጋት በሁሉም እያረጁ ባሉ ድልድዮቻችን ላይ እንደገና ቅድሚያ መስጠት እና መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ እንደ መቀስቀሻ ደወል መቀጠል አለበት። በውሃ መስመሮች እና በሸለቆዎች በተጠረበች እያደገች ባለች ከተማ ውስጥ፣ በህዝባችን እና በኢኮኖሚያችን የታመኑባትን የበርካታ የሲያትል ድልድዮችን በቅድሚያ መጠገን ቅድሚያ መስጠት አለብን።”
የግብረ ኃይሉ ተባባሪ ሊቀመንበር ፓውሊና ሎፔዝ (Paulina Lopez) “በማህበረሰብ ግብረ ሃይሉ ስም ተወክዬ በዚህ ሂደት ውስጥ ለከተማው ግልፅነት ያለንን አድናቆት ማካፈል እፈልጋለሁ” ብለዋል። “ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት ውስጥ ድልድዩን ከመጠገን በተጨማሪ፣ በሰፈር ደረጃ የደህንነት ስራ እና ከከተማው ለህብረተሰባችን አባላት እና ለአነስተኛ ንግዶች የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አይተናል። ድልድዩ እንደገና ሊከፈት ጥቂት ሳምንታት ብቻ በመቅረታችን በጣም ደስ ብሎናል።”
“እንደሌላው የምዕራብ ሲያትል ከተማ፣ እኔም ከተቀረው ከተማ ጋር እንደገና በጥቂቱ ለመገናኘት እያላመጥኩኝ ነው። ከቤተሰቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከሥራችን እና ከራሳችን ጋር የመረጥነውን ለማድረግ እውነተኛ ጊዜን እንቆጥባለን” ሲሉ የቀድሞ የሲያትል ከንቲባ እና የግብረ ሃይል ተባባሪ ሊቀመንበር ግሬግ ኒኬልስ (Greg Nickels) ተናግረዋል። “ድልድዩ በመጨረሻ ክፍት እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሚሆን በማወቅ ዙሪያ ህይወታችንን ማቀድ ልንጀምር እንችላለን። ይህ ቀን እንዲሳካ ላደረጉት እና ከመጋቢት 23 ቀን 2020 ጀምሮ በዚያ ለተጓጐሉትና ትዕግስት ላሳዩት ሁሉ እናመሰግናለን!”