
_____
ማጠቃለያ
- ባለፉት 18 ወራት ከእርስዎ እና ከጎረቤቶችዎ የሰማነውን የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ረቂቁ ውስጥ አካትተናል።
- ረቂቅ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) በሲያትል ውስጥ በሚኖሩ፣ በሚሰሩ እና በሚጫወቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች የተረዱ የሲያትል ጎዳናዎች፣ የእግረኛ መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች የወደፊት የ20 ዓመት ራዕይ ነው።
- በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ የመስመር ላይ ተሳትፎ ማእከል ላይ ስለ STP ረቂቅ መማር እና እቅዱን መገምገም የሚችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።
- ስለ STP ቪዲዮዎችን ይመልከቱ
- STPውን በጨረፍታ ይመልከቱ
- ሙሉውን የ STP ረቂቅ ይከልሱ
- የSTP ረቂቁን ከገመገሙ በኋላ፣ ለማሻሻል እንድንችል ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። ግብረ መልስዎን እስከ ጥቅምት 23 ይጋሩ!
_____
ባለፉት 18 ወራት ውስጥ ከእርስዎ እና ከጎረቤቶችዎ የሰማነውን የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ (STP) ረቂቅ ለማዘጋጀት ተጠቅመንበታል።
የሁሉንም ሰው ፍላጎት የሚያንፀባርቅ የመጓጓዣ እቅድ ለመፍጠር ከሁሉም የማህበረሰብ አባላት በተለይም ከዚህ ቀደም ተሰሚነት ካልነበራቸው አባላት ለመስማት ፈልገናል። በሺዎች የምትቆጠሩ እናንተ ልምዶቻችሁን፣ እሴቶቻችሁን፣ ተግዳሮቶቻችሁን እና ሃሳቦችን ለመካፈል ወደ ፊት መጥታችኋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ እያንዳንዳችሁ አስተያየታችሁን እና ሃሳቦቻችሁን ያካፈላችሁንን ሁሉ እናመሰግናለን! እናንተ ያቀረባችሁት ግብአት የሲያትል የመጓጓዣ እቅድን ረቂቅ ለመቅረጽ ረድቷል።
- የእኛን የደረጃ 1 ተሳትፎ ማጠቃለያ ዘገባ ይመልከቱ
- እርስዎ እና ጎረቤቶቻችሁ በእኛ የደረጃ 1 በይነ-ተገናኝ የካርታ ስራ መሳሪያ ላይ ያጋራችሁትን ይገምግሙ
- የእኛን የደረጃ 2 ተሳትፎ ማጠቃለያ ዘገባ ይመልከቱ
- እርስዎ እና ጎረቤቶቻችሁ በእኛ የደረጃ 2 በይነ-ተገናኝ የካርታ ስራ መሳሪያ ላይ ያጋራችሁትን ይገምግሙ
አሁን፣ የSTP ረቂቁን እንድትከልሱት እና ግብአት እንድታካፍሉ እየጠየቅንዎት ነው! ስለ እቅዱ የሚማሩባቸው ብዙ መንገዶች አሉ – ቪዲዮዎችን በመመልከት ወይም ቪዲዮዎችን በማዳመጥ፣ በአንድ ክስተት ላይ በመገኘት፣ የ STP ማጠቃለያ ዘገባን በመገምገም ወይም ሙሉውን እቅድ በማንበብ።
ስለ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ረቂቅ ለመማር እና ለመገምገም የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ የመስመር ላይ ተሳትፎ ማዕከልን ይጎብኙ። 10 ደቂቃ፣ 20 ደቂቃ፣ ወይም ከአንድ ሰአት በላይ እንኳ ቢኖርዎት፣ ለመሳተፍ እና የርስዎን ግብአት የሚጋሩባቸው ብዙ መንገዶች አሉ:
- ስለ STP ቪዲዮዎችን ይመልከቱ
- STPውን በጨረፍታ ይመልከቱ
- ሙሉውን የ STP ረቂቅ ይከልሱ
ስለ STP የበለጠ ይወቁ:
- ለሲያትል የመጓጓዣ እቅድ የኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ
- የባለብዙ ቋንቋ ድህረ ጣቢያችንን ይጎብኙ
- ባለብዙ ቋንቋ የስልክ መስመራችን ይደውሉ: (206) 257-2114
- በመረጡት ቋንቋ በ STP@seattle.gov ኢሜይል ለኛ ይላኩልን