Find Posts By Topic

የባላርድ ድልድይ ቅዳሜና እሁድ መዝጋት፣ ማሻሻያዎች በዚህ የፀደይ ወቅት እንደገና ይካሄዳሉ

Click here to read this blog post in English.

የሠራተኛ ቡድኖች ባለፈው የበልግ ወቅት ድልድይ በተዘጋበት ወቅት ባላርድ ድልድይ ላይ ባለው የማስፋፊያ መገጣጠሚያ ዙሪያ አዲስ ኮንክሪት አፍስሰዋል። ፎቶ:- ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
የሠራተኛ ቡድኖች ባለፈው የበልግ ወቅት ድልድይ በተዘጋበት ወቅት ባላርድ ድልድይ ላይ ባለው የማስፋፊያ መገጣጠሚያ ዙሪያ አዲስ ኮንክሪት አፍስሰዋል። ፎቶ:- ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)

የብሎግ ስታትስቲክስ:- 950 ቃላት | 5-ደቂቃ ንባብ

በጨረፍታ:-

  • ጠቃሚ የድልድይ ጥገና እና እንዳለ ለማቆየት የጥበቃ ስራን ለማጠናቀቅ በዚህ የፀደይ ወቅት በተመረጡ ቅዳሜና እሁድ የባላርድ ድልድይን እንዘጋለን።
  • የሚነዱ ከሆነ፣ በፍሪሞንት ድልድይ ላይ መጨናነቅን ለማስወገድ የ አውሮራ ድልድይ መውሰድ አለብዎት።
  • የመጀመሪያው የሳምንት መጨረሻ መዘጋት ለየካቲት 25-28 ተይዟል።
    • አርብ የካቲት 25:- የመስመር መዘጋት ከቀኑ 7 ሰአት ላይ ይጀምራል፣ እና ድልድዩ ሙሉ በሙሉ በ10 ሰአት ከምሽቱ ይዘጋል።
    • ሰኞ፣ የካቲት 28:- ድልድዩ ከንጋቱ በ 5 ሰዓት እንደገና ይከፈታል።
  • የወደፊት መዘጋት:- በእነዚህ ቀናት ተጨማሪ መዘጋቶችን በሚከተሉት ዕለተ ቀናት ይዘናል:-
    • ግንቦት 9-12
    • ግንቦት 30 – ሰኔ 2
    • ሰኔ 6-9
    • እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ፣ ለሰኔ 13-16 እና ለሐምሌ 18-21 ደግሞ የተያዙ የመጠባበቂያ ቀኖች አሉን።
  • የእኛን እቅዶች እያጠናቀቅን ስንሄድ እነዚህን ተጨማሪ የመዘጋት ቀናት አስቀድመን እናረጋግጣለን።
  • በመዘጋቱ ወቅት፣ በሊሪ ዌይ ድልድይ (ያው ከባላርድ ድልድይ በስተሰሜን) ላይም ደግሞ እንሰራለን።
  • የባላርድ ድልድይ ተዘግቶ ሳለ ምን እንደሚጠብቁ እና እንዴት በሌላ አቅጣጫ እንደሚዞሩ በዚህ የብሎግ ልጥፍ የበለጠ ይወቁ።
  • ከቡድናችን ከሁሉ ይልቅ ቅርብ ጊዜ የሆነውን ዝርዝሮችን ለማግኘት ለኢሜይል ዝመናዎች ይመዝገቡ እና የፕሮጀክት ድህረገጹን ይጎብኙ።

ባለፈው በልግ በዝናብ ምክንያት የዘገየውን ስራ ለመጨረስ፣ ባላርድ ድልድይ በዚህ የፀደይ ወራት ውስጥ በርካታ ቅዳሜና እሁድ መዝጋት አለብን። በባላርድ ድልድይ እና በአቅራቢያው ባለው የሊሪ ዌይ ድልድይ ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በብቃት መስራት መቻልን ለማረጋገጥ ሙሉ መዘጋቶች ያስፈልጉናል። ይህ ሥራ የ 15th Ave W/NW እና የባላርድ ድልድይ ንጣፍ ሥራ እና ደህንነት ፕሮጀክት (Ballard Bridge Paving & Safety Project) አካል ነው።

እነዚህ መዘጋቶች እንደ እርስዎ ላሉ ተጓዦች ምቾት የሚነሱ ቢሆኑም፣ የእርስዎን ትዕግስት እና መረዳት እናመሰግናለን። ደህንነቱ ካልተጠበቀ በስተቀር በእግር ለመሄድ፣ ብስክሌት ለመጋለብ፣ ባለ ቀላል ሞተር ብስክሌት፣ ወይም ለማንከባለል ለእርስዎ ድልድዩን ክፍት እናደርጋለን።

ባላርድ ብሪጅ የሳምንት መጨረሻ መዝጊያ ዝርዝሮች

በሚያዝያ ወር ምን እንደሚጠበቅ

  • የመጀመሪያው የሳምንት መጨረሻ መዘጋት ለየካቲት 25-28 ተይዟል።
    • አርብ የካቲት 25የመስመር መዘጋት ከቀኑ 7 ሰአት ላይ ይጀምራል፣ እና ድልድዩ ሙሉ በሙሉ በ10 ሰአት ከምሽቱ ይዘጋል።
    • ሰኞ፣ የካቲት 28 ድልድዩ ከንጋቱ በ 5 ሰዓት እንደገና ይከፈታል።

በኋላ በዚህ ጸደይ ወቅት ምን እንደሚጠበቅ

  • በእነዚህ በሚከተሉት ዕለተ ቀናት ተጨማሪ የሳምንት መጨረሻ መርሐግብር አውጥተናል:
    • ግንቦት 9-12
    • ግንቦት 30 – ሰኔ 2
    • ሰኔ 6-9
    • እንዲሁም አስፈላጊም ከሆነ፣ ከሰኔ 13-16 እና ጁላይ 18-21 ደግሞ የተያዙ የመጠባበቂያ ቀናት አሉን።
  • የእኛን እቅዶች እያጠናቀቅን ስንሄድ እነዚህን ተጨማሪ የመዘጋት ቀናት አስቀድመን እናረጋግጣለን።
  • የእያንዳንዱ መዘጋት ጊዜ፣ ከአርብ ምሽት እስከ ሰኞ ጥዋት ድረስ ተመሳሳይ ይሆናል።

እንዴት መረጃን እያገኙ እንደሚቆይ

  • እርስዎ ከሁሉ ይልቅ የቅርብ ጊዜ የሆነውን የግንባታ መረጃ እንዲያገኙ የእኛን የኢሜይል ዝመናዎች ለመቀበል እዚህ ይመዝገቡ
  • እኛ በታቀደው መሰረት የመዘጋቱ እቅድ መፈጸሙን፣ ወይም መሰረዙን ለማረጋገጥ፣ ለእያንዳንዱ መዘጋት እቅዱን በሳምንት አጋማሽ ዝመና እናረጋግጣለን፣ እና አርብ የመጨረሻ የተዘመነውን መዘጋት እንልካለን።

 

እባክዎን ያስተውሉ፡ እነዚህ ቀናት እና ሰዓቶች በአየር ጠባይ ሁኔታዎች ምክንያት፣ በሰራተኞች እና በቁሳቁሶች መኖር ወይም በሌሎች ሁኔታዎችም ምክንያት ሊለወጡ ይችላሉ

ተዝግቶ ባለ ወቅት መዘዋወር

በእግር የሚሄዱ እና ብስክሌት የሚጋልቡ ሰዎች

  • ባላርድ ድልድይ ለአሽከርካሪዎች ዝግ ሲሆን እርስዎ በእግረኛ መንገድ ላይ በእግር መሄድ ወይም በብስክሌት መጓዝ ይችላሉ።
  • ለደህንነት ሲባል የእርስዎን ብስክሌት በእግር እንዲገፉ ሊጠየቁ ይችላሉ።
  • ለደህንነት ሲባል ደግሞ እርስዎ ከድልድዩ በሌላ በኩል ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞሩ ሊደረግ ይችላል።

አሽከርካሪዎች እና ጭነት

  • እርስዎ እየነዱ ከሆነ፣ እባክዎትን አውሮራ ድልድይን (SR 99) ከሁሉ ይልቅ እንደ አስተማማኝ በሌላ አቅጣጫ የማዞሪያ መንገድ ይጠቀሙ።
  • በድልድዩ የአቅም ውስንነት ምክንያት፣ እርስዎ ወደ ፍሪሞንት ወይም ዌስትሌክ የሚጓዙ ከሆነ የፍሪሞንት ድልድይ ብቻ እንዲጠቀሙ ይመከራሉ።
  • በተዘጋ ጊዜ እርስዎን ተለዋጭ የጉዞ መስመሮች እንዲመራዎት ለመርዳት በባላርድ ድልድይ ዙሪያ ወደ ሌላ አቅጣጫ የማዞሪያ ምልክቶችን ማየት ይችላሉ። እባክዎትን እርስዎ ወደ ባላርድ ድልድይ ሳይደርሱ በፊት ወደ ሌሎች መስመሮች ይዙሩ።

የአውቶቡስ ተሳፋሪዎች

  • በተለመደ ወቅት የባላርድ ድልድይን የሚጠቀሙ አውቶቡሶች በሌላ አቅጣጫ እንደገና ወደ ፍሬሞንት ድልድይ ስለሚዞሩ ስለሚችሉ ረዘም ያለ የአውቶቡስ ጉዞዎችን መጠበቅ አለብዎት።
  • እባክዎን በባላርድ ድልድይ አቅራቢያ ያሉ አንዳንድ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች ለጊዜው መዘጋቶቹን ለመደገፍ ወደ ሌላ ቦታ ሊዛወሩ እንደሚችሉ ይወቁ።
  • የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የአገልግሎት ምክሮችን በመከታተል እና ለመጓጓዣ ማንቂያዎች በመመዝገብ በአካባቢው ስላለው የመጓጓዣ አገልግሎት መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

በጀልባዎች ለሚሳፈሩ

  • በጀልባ የሚጓዙ ከሆነ፣ ከባላርድ ድልድይ ስር መጓዙን መቀጠል ይችላሉ።
  • በጀልባ በሚጓዙበት ጊዜ የሁሉንም ሰው ደህንነት ለማረጋገጥ እባክዎትን የእርስዎን አካባቢ ይገንዘቡ።

 

የመዘጋት ካርታ

በዚህ የፀደይ ወቅት በተወሰኑ የሳምንት መጨረሻዎች ላይ የባላርድ ድልድይ መዘጋት አካባቢ ያለው ካርታ። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
በዚህ የፀደይ ወቅት በተወሰኑ የሳምንት መጨረሻዎች ላይ የባላርድ ድልድይ መዘጋት አካባቢ ያለው ካርታ። ንድፋዊ ምስል:- የሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)

 

ለእርስዎ የጉዞ መርጃ ምንጮች

ድልድዩ ተዘግቶ ባለበት ወቅት፣ ለመዘዋወር ከታች የተዘረዘሩትን አማራጮች ከግምት ያስገቡ። በአካባቢው ውስጥ መገብየትም ይችላሉ – በግንባታ ወቅት የባለርድ ንግዶች ክፍት ናቸው።

ጥቂት የጉዞ አማራጮች እዚህ እነሆ:-

ከሌሎች የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር ማቀነባበር

የእርስዎን ለመዘዋወር እና በተቻለ መጠን የጉዞ ተጽእኖዎችን እንዲቀነስ ለመርዳት በአካባቢው ከሚገኙ በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ አብረን እየሰራን ነው።

ለተጨማሪ ዝርዝሮች የእነዚህን የፕሮጀክት ድህረ-ገጾች እርስዎ እንዲጎበኙ እናበረታታዎታለን:-

መረጃ እንዳገኙ ይቆዩ