ማወቅ ያለብዎ:
- በመከር ወቅት እኛ የምንኖርበትን ወይም የንግድ ባለቤት የሆንበትን የእግረኛ/ የጐን መንገዶቻችንን፣ የአትክልት መስመሮቻችንን፣ እና አሸንዳዎቻችንን በማፅዳት ሁላችንም የበኩላችንን ማድረግ አለብን።
- ምንም እንኳን ክረምቱ ገና ሩቅ ቢመስልም – ለበረዶ፣ ለጠጣር በረዶ ሁኔታዎች ከመድረሳቸው በፊት አሁን መዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
በዚህ ዓመት የጐን የእግረኛ መንገድ እርጥብ ወይም በረዶ በሚሆንበት ጊዜ የመንሸራተት አደጋ እንዳይሆን ለመከላከል የወደቁ ቅጠሎችን ለማፅዳት መርዳት የእያንዳንዱ ሀላፊነት ነው።
ቅጠሎችን መጥረግ ሁሉም ሰው መጓጓዝ እንዲችል የእግረኛ መንገዱን ደህንነት የተጠበቀ እና ተደራሽ ያደርገዋል፣ በተለይም የተደራሽነት ችግር ላላቸው ወይም ለመጓጓዝ አስቸጋሪ ጊዜ ያላቸው ሰዎች። በጐረቤትነት ብቻ የሚደረግ አይደለም – ሕግም ነው። ከመንገድዎ ጠርዝ እና ከንብረትዎ መስመር መካከል ያለው ቦታ፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ የመትከያ ቦታዎችን እና እፅዋትን ጨምሮ የመጠበቅ ኃላፊነት የርስዎ ነው።
የተዘጉ አሸንዳዎችን መጥረግ አይርሱ! የፍሳሽ ማስወገጃ/ አሸንዳ ከታገደ እና የዝናብ ውሃ በትክክል ሊፈስ የማይችል ከሆነ፣ ሰዎች የሚራመዱበት እና በማንከባለል የሚጠቀሙት፣ በተለይም በመንገዶች ጠርዝ መወጣጫዎች ታችኛው ክፍል አካባቢ በጎርፍ ሊጥለቀለቅ ይችላል። ይህ በእጅ የተሽከርካሪ ወንበሮችን ለመጠቀም የመንገዶች ጠርዝ መወጣጫውን አስቸጋሪ ወይም የማይቻል ያደርገዋል። ስለዚህ እባክዎን ያስታውሱ፣ ቅጠሎችን በሚያጸዱበት ጊዜ፣ እባክዎን ወደ አሸንዳው ውስጥ እንዳይገቡ ያረጋግጡ። ቅጠሎችን በአረንጓዴ ምግብዎ እና በጓሮ ማጠራቀሚያዎችዎ ውስጥ ማስገባት ጥሩ ነው።
ቅጠሎችዎን እንዴት፣ መቼ፣ እና የት በቅጠል መጥረጊያ ማጠራቀም እና ንብረትዎን እንደሚያፀዱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ መ/ ቤት (SDOT) ብሎግ ልጥፍ ይመልከቱ።
ምንም እንኳን ክረምቱ ገና ሁለት ወራት ቢቀረውም፣ ለእነዚህ የበረዶ፣ እና የጠጣር በረዶ የክረምት አየር ሁኔታዎች ከመድረሳቸው በፊት አሁን መዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
ቀደም ብለን እንደገለጽነው፣ በሲያትል ያለው ክረምት ከባድ ዝናብ፣ ከፍተኛ ንፋስ፣ በረዶ እና ጠጣር በረዶ ሊያመጣ ይችላል (ያለፈውን ክረምት ትልቁን የበረዶ አውሎ ንፋስ ያስታውሱ?) ዓመቱን በሙሉ ለበረዶ እንዘጋጃለን። መንገዶቹን ከወደቁ ዛፎች እና ቅርንጫፎች እስከ በረዶ እና ጠጣር በረዶ ሁሉንም ነገር ግልፅ ለማድረግ፣ መንገዶቹ ለስላሳ እንዲሆኑ ጉድጓዶችን ማስተካከል እና በከተማው ውስጥ ምልክቶችን እና የመብራት ምልክቶችን በመጠገን እንሰራለን።
እንዲሁም የክረምት አውሎ ነፋሶች በሚቀርቡበት ጊዜ ደህንነትዎ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁኔታዎችን እንከታተላለን። ከፍተኛ ነፋሳት፣ ከባድ ዝናብ፣ ወይም በረዶ እና ጠጣር በረዶ ትንበያው ውስጥ ሲሆኑ ሰራተኞቻችን ወደ ሥራ ለመሄድ ዝግጁ ናቸው! እንዲሁም የጨው እና ፈሳሽ ፀረ-በረዶ ማቅረቢያዎቻችን ተከማችተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
እኛ እየተዘጋጀን ነው፣ እና እርስዎም እንዲሁ ማድረግ አለብዎት! አውሎ ነፋሱ ከመምጣቱ በፊት ለመዘጋጀት – እና ከድርጊቱ አስቀድመው – ማድረግ የሚችሉት እዚህ አለ –
- ከሲያትል የበረዶ መንገዶች ጋር ይተዋወቁ። እርስዎ መሄድ ወደሚያስፈልግዎት ለመድረስ በጣም አስተማማኝ መንገድ እንዲሆን፣ እነዚህ እኛ ለማፅዳት ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጎዳናዎች ናቸው። አንዴ በረዶ ከጣለ፣ የትኞቹን መንገዶች የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ መ/ ቤት (SDOT) ጠርጐ እንደሆነ እና የአሁኑ የመንገድ ሁኔታዎች የቀጥታ የካሜራ ስርጭቶች መኖራቸውን ቅጽበታዊ ዝመናዎችን ለማየት ይህንን የመስመር ላይ የአውሎ ነፋስ ምላሽ ካርታ ይጠቀሙ።
- በማዕበል ጊዜ ማን ለመንቀሳቀስ እርዳታ ሊያስፈልገው እንደሚችል ለማየት ከጎረቤቶችዎ ጋር ይነጋገሩ እና በቀኝ እና በግራ መንገዶች መካከል ባለው ስፋት ላይ ያሉት ሁሉም የእግረኛ መንገዶች በአካፋ መጠረጋቸውን እቅድ ያውጡ። የመኪና መግቢያ መንገድዎን እና የየእግረኛ መንገድዎን ለማፅዳት እገዛ ከፈለጉ፣ ማንን እርዳታ መጠየቅ እንደሚችሉ ያስቡ።
- ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት/ ጥያቄ ከማድረጋቸው በፊት ሞቅ ያለ ልብሶችን፣ ተጨማሪ ብርድ ልብሶችን፣ እና የእጅ ባትሪዎችን ያከማቹ።
- በረዶን እና ጠጣር በረዶን ለማጽዳት የበረዶ አካፋ እና የጎዳና ጨው ከረጢት ያግኙ።
- የመጀመሪያ እርዳታ ስብስቦችን እና የሶስት ቀን የምግብ፣ የውሃ እና የመድኃኒት አቅርቦቶች እንዳልዎት ያረጋግጡ።
ከሲያትል ፓርኮች እና መዝናኛ ወዳጃዊ የደህንነት ማሳሰቢያ እዚህ አለ:
ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በሚከሰትበት ጊዜ፣ በተለይም ኃይለኛ ነፋስ ሲኖር፣ እባክዎን በጣም በደን ከተሸፈኑ አካባቢዎች ይራቁ።
ከሲያትል ከተማ መብራት ጥቂት “የዛፎች ምክሮች” በጥቂቱ እነዚህ ናቸው:
አብዛኛዎቹ ቅጠሎች ወደቀው፣ የዛፎችዎን ቁመና ለመመርመር ጥሩ ጊዜው አሁን ነው። ሊጠበቁ የሚገባቸው ጥቂት ምክሮች እዚህ አሉ:
- በአውሎ ነፋስ ወቅት የተሰባበሩ ወይም ተሰነጣጥቀው ሊወድቁ የሚችሉትን ቅርንጫፎች ይመልከቱ።
- በመብራት ኃይል መስመሮች ላይ የሚተሻሹትን የዛፍ ቅርንጫፎች በዓይነ ቁራኛ ይከታተሉ።
- ከወረዱ የኤሌክትሪክ መስመሮች መራቅዎን ያስታውሱ። የወደቁ የኤሌክትሪክ መስመሮች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ 9-1-1 ይደውሉ።
ዛፎችዎ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የደህንነት ችግሮች ሊያስከትሉ የሚችሉ ከሆነ፣ የሚያሳስብዎትን ነገሮች ለመገምገም የሲያትል ከተማ መብራት የአትክልት ሥራ ክፍልን በመስመር ላይ ይገናኙ ወይም በስልክ (206) 386-1733 ይደውሉ። የትርጉም አገልግሎት ነጻ ነው። አንዴ ዛፎችዎ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ካወቁ፣ በሚያምር የክረምት የፀሀይ መጥለቂያዎችን የእነሱን ረቂቅ ትይዩዎች መደሰት ይችላሉ!