Please note: you can return to the English version of this blog post, by clicking here.
ማጠቃለያ:
- ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር በመተባበር የአውቶቡስ ብቻ መስመሮችን በመጨመር በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የሕዝብ ማመላለሻን ይበልጥ አስተማማኝ እያደረግን ነው። የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች አውቶቡሶችን ከሌሎች ተሽከርካሪዎች በመለየት በሕዝብ ማመላለሻ ላይ የሚጓዙ ሰዎች እንዲንቀሳቀሱ ይረዳሉ።
- በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ሁሉ የሕዝብ ማመላለሻ ተሰፈሪዎች ከፍተኛ ሆኖ ስለቆዩ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የአውቶቡስ መስመሮችን እየጨመርን ነው።
- በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ በሕዝብ ማመላለሻ የሚጓዙ ሰዎች የአዲሱ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች አንዴ ከተሠሩ በኋላ ጥቅሞችን ያያሉ። በተለይም በከባድ ትራፊክ ውስጥ፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የሕዝብ ማመላለሻ የሚሳፈሩ ሰዎች የጉዞ ጊዜን ይቀንሳሉ። ይበልጥ አስተማማኝ የአውቶቡስ የጉዞ ጊዜዎች በሲያትል ውስጥ ለሚጓዙ ሰዎች የሕዝብ ማመላለሻን መሳፈር የተሻለ ምርጫ ያደርገዋል።
- የ Rainier Ave S Vision Zero ፕሮጀክት አካል እንደመሆኑ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ላለፉት በርካታ አመታት የደህንነት ማሻሻያዎችን እያደረግን ነው። በቅርብ ጊዜ፣ የመስመር 7 ትራንዚት-ፕላስ መልቲሞዳል ኮሪደር (Transit-Plus Multimodal Corridor) ፕሮጀክት አካል በመሆን በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ሌሎች የደህንነት እና መገናኛ ማሻሻያዎችን መገንባት ጀመርን።
- የሲያትል የሕዝብ ማመላለሻ መለኪያን (Proposition 1) 80 በመቶ የሲያትል መራጮች ማሳለፋቸው ምስጋና ይግባውና በራኒየር አቬኑ ደቡብ ላይ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን እየጨመርን ነው። በህዳር 2020 ውስጥ የፀደቀው፣ ለውሳኔ የቀረበው (Proposition) 1 በከተማችን ውስጥ ላሉ ተደጋጋሚ፣ አስተማማኝ እና ተደራሽነት ያለው የአውቶቡስ አገልግሎት የገቢ ምንጭ ፈጥሯል። በ0.15% የሽያጭ ታክስ (በ$100 ዶላር ንጥል ከ15 ሳንቲም ጋር እኩል የሆነ) በማህበረሰብዎ ውስጥ የሕዝብ ማመላለሻ መዳረስ አገልግሎትን እየደገፉ ነው።
ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር በመተባበር የአውቶቡስ ብቻ መስመሮችን በመጨመር በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የሕዝብ ማመላለሻን ይበልጥ አስተማማኝ እያደረግን ነው።
የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች አውቶቡሶችን ከሌሎች ተሽከርካሪዎች በመለየት የሕዝብ ማመላለሻ የሚሳፈሩትን ሰዎች ይበልጥ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ይረዳሉ። በተለይም በከባድ ትራፊክ ውስጥ፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የሕዝብ ማመላለሻ የሚሳፈሩ ሰዎች የጉዞ ጊዜን ይቀንሳሉ።
ማን ሊጠቀምባቸው እንደሚችል እና ሌሎች ዝርዝሮችን ጨምሮ ስለ አውቶቡስ-ብቻ መስመሮች ዓይነቶች በሕዝብ ማመላለሻ መስመር ድረ-ገጻችን ላይ ይወቁ።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በመስመር 7 ላይ የሕዝብ ማመላለሻ ተሳፋሪነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቆይቷል። በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የአውቶቡስ መስመሮችን ከምንጨምርባቸው ምክንያቶች አንዱ በመስመር 7 ላይ የሚተማመኑ የሕዝብ ማመላለሻ ተሳፋሪዎችን በተሻለ መንገድ ለማገልገል ነው።
በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ያለው መስመር 7 በሲያትል በጣም ከሚበዛባቸው የአውቶቡስ መስመሮች አንዱ ነው፣ በቀን ወደ 8,000 የሚጠጉ ተሳፋሪዎችን በማገልገል (ከወረርሽኙ በፊት በቀን 11,200 ተሳፋሪዎች)። በሪኒየር ሸለቆ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በየቀኑ መስመር 7 ላይ ጥገኛ ናቸው። ሰዎች ወደ ትምህርት ቤቶች አውቶቡስ ይሳፈራሉ፣ የመዋእለ ሕጻናት ማእከላት፣ የግሮሰሪ መደብሮች፣ ስራዎች እና የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ቦታዎች።
በሲያትል ሁሉ ውስጥ፣ ብዙ ሰዎች ወደሚፈልጉበት ቦታ ለመድረስ እና መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት በየቀኑ በሕዝብ ማመላለሻ ላይ ይተማመናሉ። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሁሉ ሰዎች በሕዝብ ማመላለሻ ላይ መተማመናቸውን ቀጥለዋል። ይበልጡን ቀለም ባላቸው ሰዎች ሰፈሮች የሚያገለግሉ መስመሮችን ጨምሮ የሕዝብ ማመላለሻ በበርካታ መስመሮች በከፍተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ቆይቷል። ከተማዋ ከወረርሽኙ ወደ ፊት ስትሄድ እነዚህ ማህበረሰቦች ምቹ እና አስተማማኝ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል። በጣም በሚያስፈልጉበት ቦታ ላይ በመዋዕለ ንዋዮች እንድናተኩር አስፈላጊያችን ነው። ይህን ማድረግ ከዋና እሴቶቻችን እና ግቦቻችን ጋር በማመላለሻ ፍትሃዊ እኩልነት እና ደህንነት ዙሪያ ያስማማል።
የ Rainier Ave S Vision Zero ፕሮጀክት አካል በመሆኑ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ላለፉት በርካታ አመታት የደህንነት ማሻሻያዎችን እየገነባን ነው። በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ደህንነትን ለማሻሻል የእኛ ስራ ገና አላለቀም። ወደፊት ተጨማሪ የደህንነት ማሻሻያዎችን ለማድረግ ወደዚህ መንገድ ቀጥለን ለመመላለስ አቅደናል። በቅርብ ጊዜ፣ የመስመር 7 ትራንዚት-ፕላስ መልቲሞዳል ኮሪደር (Transit-Plus Multimodal Corridor) ፕሮጀክት አካል በመሆን በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ሌሎች የደህንነት እና መገናኛ ማሻሻያዎችን መገንባት ጀመርን።
በሪኒየር ጎዳና ደቡብ አኳያ ላይ መጪው የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የሚሰሩት ስራዎች በሁለት ደረጃዎች ይከናወናሉ፣ የመጀመሪያው ደረጃ ግንባታ ከሐምሌ 8 – 10 ይካሄዳል።
በዚህ በጋ፣ ስለ ሁለተኛው የስራ ደረጃ የበለጠ መረጃ ለማካፈል እና የማህበረሰብ አስተያየቶችን ለመሰብሰብ በማህበረሰቡ ውስጥ እንሆናለን።
የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ:
- ደረጃ 1: ሐምሌ መጀመሪያ ላይ፣ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚጓዝ አውቶቡስ-ብቻ መስመር ለመጨመር በደቡብ አላስካ ጎዳና እና ደቡብ ዋልደን ጎዳና መካከል ግንባታ እንጀምራለን። እንዲሁም በደቡብ ኦርገን ጎዳና እና ደቡብ ኤድመንድስ ጎዳና መካከል ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚሄድ አውቶቡስ-ብቻ መስመር እንጨምራለን። የኩርባ ዳር የጉዞ መስመርን እናስወግደው እና ወደ አዲስ የአውቶቡስ ብቻ መስመር እንቀይረዋለን። ሁሉንም ነባር የመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያዎችን፣ ባለሁለት መንገድ መሃል መታጠፊያ መስመርን እና የጭነት መዳረሻን ሁሉ እንዳሉ እንጠብቃቸዋለን።
- ግንባታው ከሐምሌ 8 – 10 እንዲሆን ታቅዷል። ይህ ሥራ በአየር ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እና ሊለወጥ የሚችል ነው። መንገዱ በግንባታ ወቅት ክፍት ሆኖ ይቆያል፣ እና ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የመስመር መዘጋት ሊጠብቁ ይችላሉ።
- ደረጃ 2: ከደቡብ ዋልደን ጎዳና እስከ ደቡብ ማሳቹሴትስ ጎዳና ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚጓዝ አውቶቡስ ብቻ መስመር የሚዘረጋውን የደረጃ 2 ፕሮጀክት እያጠናን ነው።
- 2022 በጋ: ስለዚህ ፕሮጀክት መረጃን ለማካፈል እና የእርስዎን ግብረ መልስ ለመስማት ማህበረሰቡን እንደርሳለን። የእርስዎ ግብረ መልስ የደረጃ 2 የፕሮጀክት ንድፍ ለማሳወቅ ይረዳል። የፕሮጀክት ንድፍ እስከ 2023 ድረስ ይቀጥላል።
ዛሬ: መደበኛ የተለመደ ነባር የመንገድ ንድፍ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ክፍል (ወደ ሰሜን የሚታይ)፣ በደረጃ 1 ፕሮጀክት አካባቢ
ወደፊት፡ የተለመደ የመንገድ ንድፍ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ (ወደ ሰሜን የሚመለከተው) ክፍል፣ በደረጃ 1ፕሮጀክት አካባቢ። የአንድ ወደሰሜናዊ አቅጣጫ ያለው የጉዞ መስመር ወደ አውቶቡስ–ብቻ መስመር ሽግግር ያሳያል።
ከዚህ በታች የተገለጹት፣ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የሕዝብ ማመላለሻ የሚሳፈሩ ሰዎች ከአዲሱ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች ብዙ ጥቅሞችን ያያሉ።
ከሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ ያለው የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የሚጠበቀው የፕሮጀክት ጥቅሞች:
- በምትጠብቀው ጊዜ የሚመጣው በሪኒየር ጎዳና ደቡብ ላይ የበለጠ አስተማማኝ የሕዝብ ማመላለሻ። ይህ እንደ መስመር 7፣ 48 እና 106 ያሉ ከፍተኛ ተሳፋሪነት ያላቸውን ተደጋጋሚ የአውቶቡስ መስመሮችን ያካትታል
- ወደ ተራራ ቤከር ቀላል ባቡር ጣቢያ እና ከማክሌላን ጎዳና ሜትሮ ትራንዚት ጣቢያ ጋር ቀላል ግንኙነቶች። በ2023 ከሚከፈተው አዲሱ የጁድኪንስ ፓርክ ቀላል የባቡር ጣቢያ (Judkins Park Light Rail Station) ጋር ቀለል ያሉ ግንኙነቶችም ይኖራሉ።
- በጠዋት የአውቶቡስ ጉዞ ላይ በአማካይ የ2 ደቂቃ የጉዞ ጊዜን መቆጠብ። ሁኔታዎች ከወትሮው በበለጠ በተጨናነቁበት ወቅት የጠዋት ጉዞ ጊዜ 6 ደቂቃዎችን መቆጠብ
- በደቡብ አላስካ ጎዳና እና ደቡብ ዋልደን ጎዳና መካከል ወደ ሰሜን ሲጓዙ ከ1 ደቂቃ በላይ መቆጠብ
- ወደፊት፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሩን ይበልጥ ወደ ሰሜን ወደ I-90 በማስፋት ተጨማሪ የሕዝብ ማመላለሻ የጉዞ ጊዜ ቁጠባ እንጠብቃለን። በዚህ አካባቢ፣ የትራፊክ መጠኖች ከፍ ያለ እና ብዙ ጊዜ መጨናነቅ ከፍ ያለ ነው።
- ተጨማሪ ጉዞዎችን ወደ ሕዝብ ማመላለሻ በመቀየር የመንገዶቻችንን ስፋት ቅልጥፍና ለማሻሻል ይረዳል፣ ሁሉንም ይጠቅማል
አውቶቡስ-ብቻ መንገዶች ፈጣን እውነታዎች:
- የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች ለህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች የተገደቡ የጉዞ መስመሮች ናቸው። የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ማንኛውም የህዝቡ አባል ሊሳፈርባቸው እና ሊጠቀምባቸው የሚችል ተሽከርካሪዎች ናቸው። ይህ የትምህርት ቤት አውቶቡሶችን፣ የሚጋሩዋቸው መለስተኛ አውቶቡሶችን፣ የስራ ማመላለሻዎችን፣ የሞተር ብስሊለቶችን፣ የሚጋሩዋቸው መኪኖችን፣ ወይም የተኮናተሯቸው አውቶብሶችን አያካትትም።
- ብስክሌት የሚጋልቡ ሰዎች የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን እንዲጠቀሙ ተፈቅዶላቸዋል። የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን እንዲጠቀሙ ተፈቅዶላቸዋል።
- ሌሎች የአውቶብስ ብቻ መስመሮች በተወሰኑ ጊዜያት ለአውቶቡሶች ብቻ የተገደቡ ሲሆኑ፣ አንዳንድ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች በቀን ለ24 ሰአታት ለአውቶቡሶች የተገደቡ ናቸው። የመንገድ ላይ ምልክቶች እና የሚደረጉ ምልክቶች የአውቶቡስ-ብቻ የሰዓት ገደቦችን ይገልጻሉ። ማቆሚያዎችን ጨምሮ፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች በሌሎች ተሽከርካሪዎች መጠቀም የሚቻል ከሆነ/መቼ ምልክቶች እና የሚደረጉ ምልክቶችም ይገልፃሉ።
- አብዛኛው የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች ሌሎች ተሽከርካሪዎችን የሚያሽከረክሩ ሰዎች መስቀለኛ መንገድ ጋ ለመታጠፍ ወይም ወደ ሠፈር ዉስጥ መንገድ ለመዞር ወደ መስመሩ እንዲገቡ ይፈቅድላቸዋል።
ስለዚህ ፕሮጀክት የበለጠ ይወቁ እና አስተያየትዎን ከእኛ ጋር ያጋሩ:
- በበርካታ ቋንቋዎች የ በሪኒየር ጎዳና ደቡብ አውቶቡስ-ብቻ መስመር ፕሮጀክት ድህረጣቢያን ይጎብኙ
- ስለፕሮጀክቱ መደበኛ የኢሜል ዝመናዎቻችንን ለመቀበል ይመዝገቡ
- ኢሜል ይላኩልን: TransitLanes@seattle.gov
- በመረጡት ቋንቋ አንድ የድምጽ መልእክት ይተዉ እና እኛ እንመልስልዎታለን: 206-257-2201