Please note: to return to the English version of this blog post, please click here.
ማጠቃለያ:
- ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር በመተባበር በ Rainier Ave S ሰሜን አቅጣጫ በS Alaska St እና S Walden St መካከል፣ እና በረኒየር ሸለቆ (Rainier Valley) ከS Oregon St እና S Edmunds St መካከል በቅርብ ጊዜ የአውቶቡስ ብቻ መስመሮችን ሠርተናል።
- የአውቶቡስ መስመሮቹን ለማራዘም አሁን ሁለት አማራጮችን እየገመገምን ነው። ይህ ቅጥያ በRainier Ave S ወደሰሜን ሄድ ብሎ S Walden St እና S Grand St መካከል ይሆናል።
- እባክዎን የእኛ የዳሰሳ ጥናታችንን እስከ ህዳር 13 ይውሰዱ። በቀረቡት ሁለት የቀረቡ ሀሳቦች አማራጮች ላይ፣ Rainier Ave S ላይ እንዴት እንደሚጓዙ እና የሕዝብ መጓጓዣ የመውሰድ ልምድዎን እኛ እንዴት በበለጠ ማሻሻል እንደምንችል የእርስዎን ግብአት ማጋራት ይችላሉ።
- የደረጃ 2 የRainier Ave S አውቶቡስ-ብቻ መስመር አማራጮችን ጥቅምት 25 በሚደረግ አንድ ምናባዊ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ እናቀርባለን። የስብሰባ ዝርዝሮች በድህረ-ገፃችን ላይ ይለጠፋሉ። ከስብሰባው በኋላ በፕሮጀክት ድህረ-ገጻችን ላይ የተቀዳውን እንለጥፋለን።
ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር ሸሪክ በመሆን፣ በዚህ በበጋው መጀመሪያ ላይ፣ በRainier Ave S ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ አዲስ የአውቶቡስ–ብቻ መስመሮችን ሰራን።
ይህ ከS Alaskan St እስከ S Walden St ድረስ ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚያመሩ የአውቶቡስ መስመሮችን፣ እና ከS Oregon St እስከ S Edmonds St ድረስ ወደ ደቡብ የሚያመሩ የአውቶቡስ መስመሮችን ይጨምራል። ይህን ለውጥ ከተገበርን ወዲህ የትራፊክ እና የአውቶቡስ የጉዞ ጊዜዎችን እየተቆጣጠርን አለን። በሚቀጥሉት ወራት ላይም መረጃዎችን መሰብሰብ እንቀጥላለን። እስካሁን፣ ለአውቶቡሶች የጉዞ ጊዜ ቁጠባ እየተገነዘብን ነው።
በአሁኑ ወቅት በRainier Ave S ወደ ሰሜኑ አሁን ያሉትን ነባር የአውቶቡስ መስመሮች ለማራዘም፣ ሁለት ምርጫዎችን (“አማራጮች“) በS Walden St እና በS Grand St መካከል እየገመገምን ነው።
አንዴ ሙሉ በሙሉ ከተሰራ በኋላ፣ የአውቶቡስ ተሳፋሪዎች በጥዋቱ ከፍተኛ የትራፊክ ሰዓት ሲጓዙ 5 ደቂቃ ያህል ይቆጥባሉ ብለን እንጠብቃለን።
በማህበረሰብ ግብረ መልስ ላይ በመመስረት አንድ የተሻለ ነው የሚሉትን አማራጭ እንድንመርጥ እንዲረዱን እየጠየቅን ነው።
በአሁን ወቅት በRainier Ave S ላይ እንዴት እንደሚመላለሱ እና የሕዝብ መጓጓዣ በመውሰድ የሚያደርጉትን ልምድዎን እንዴት እንድናሻሽል እንደሚፈልጉ፣ እባኮትን ሀሳቦችዎን ለማጋራት እስከ ህዳር 13 ድረስ የዳሰሳ ጥናታችንን ይውሰዱ።
እንዲሁም የበለጠ ለማወቅ ጥቅምት 25 ላይ በሚደረገው ምናባዊ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ መገኘት ይችላሉ። የስብሰባ ዝርዝሮች በድህረ-ገጻችን ላይ ይገኛሉ። ስብሰባውን እንቀርጻለን/ እንቀዳለን እና አንድ አገናኝ ድህረ-ገጻችን ላይ እንለጥፋለን።
ከታች ያሉት የሁለቱ አማራጮች አንድ አጭር ማጠቃለያ ነው።
እንዲሁም ስለ ጥቅሞቹ እና ከግምት ስለገቡ ስለ እያንዳንዱ አማራጭ ተጨማሪ ዝርዝሮችን በድረ-ገፃችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
አማራጭ 1
በዚህ አማራጭ አንድ ከS Walden St እስከ S Grand St ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያለውን መስመር ወደ አውቶቡስ መስመር እናዞራለን።
ከS Grand St እስከ S Walden St (ወደ ሰሜን በኩል ሲታይ)
አማራጭ 2
እንደ አማራጭ 1፣ በዚህ አማራጭ ከS Walden St እስከ S Grand St አንዱን ወደ ሰሜን አቅጣጫ መስመር ወደ አንድ የአውቶቡስ መስመር እንለውጣለን።
እንዲሁም በS Grand St እና S College St መካከል ያለውን የመሃል መታጠፊያ መስመር እናስወግዳለን እና ሁለት ወደ ሰሜን የሚሄዱ የጉዞ መስመሮች (በግምት 5 ብሎኮች) ይኖረናል።
ከS Grand St እስከ S College St (ወደ ሰሜን በኩል ሲታይ)
ከS College St እስከ S Walden St (ወደ ሰሜን በኩል ሲታይ)
ቀጣይ እርምጃዎች
እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በሰማነው ላይ እና ስለደረጃ 2 ፕሮጀክት ቀጣይ እርምጃዎች ተጨማሪ መረጃ እናካፍላለን። የፕሮጀክት ቅየሳው እስከ 2023 ድረስ ይቀጥላል፣ እና ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ በ2024 ሊጀመር ይችላል።
የበለጠ ለማወቅ
- ድህር: የ Rainier Ave S የአውቶቡስ-ብቻ መስመር ፕሮጀክት ድህረ ገጽን ይጎብኙ፣ በብዝሃነ ቋንቋዎች ይገኛል
- የኢሜይል ዝመናዎች: ስለ ፕሮጀክቱ መደበኛ የኢሜይል ዝመናዎችን ለመቀበል ይመዝገቡ
- ኢሜይል: TransitLanes@seattle.gov ይላኩልን
- የድምጽ መልዕክት: በመረጡት ቋንቋ የድምጽ መልዕክት ይተው እና መልሰን እንደውላለን: 206-257-2201
በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ ስለጊዜዎ እና ስላሳዩት ፍላጎት እናመሰግናለን!