Find Posts By Topic

የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ | ከንቲባ ብሩስ ሃረል (Bruce Harrell) ያቀረበው የምከር ሀሳብ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለማደጎ ወደ ከተማ ምክር ቤት ይሄዳል 

People walking in the U District neighborhood.

ማጠቃለያ 

ከሁለት አመታት የህዝብ ተሳትፎ በኋላ፣ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ የምክር ሃሳብ አዘጋጅተናል እና ዛሬ ከከተማ ምክር ቤት ጋር ተጋርተናል። 

የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ በሲያትል ውስጥ በሚኖሩ፣ በሚሰሩ እና በሚጫወቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች የተነገረለት የሲያትል መንገዶች፣ የእግረኛ መንገዶች እና የህዝብ ቦታዎች የወደፊት የ20 ዓመት ራዕይ ነው። የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለከተማችን ላሁኑ ወቅት እና ለወደፊትም የሚሰራ የመጓጓዣ ስርዓት ራዕይን፣ ግቦችን፣ ቁልፍ እንቅስቃሴዎችን እና ምክረ ሃሳቦችን መሠረት ያቋቁማል። ዕቅዱ እያንዳንዱን ከወደፊት የመጓጓዣ የድጋፍ ገንዘብ እስከ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ድረስ በሕዝብ ቦታ የምንደሰትበትን እና በከተማዋ ውስጥ የምንዘዋወርበትን መንገድ የሚያሳድጉ ሁሉንም ነገር ያሳውቃል እና ቅርጽ እንዲኖረው ያግዛል። 

የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ለሲያትል በስድስት ቁልፍ ግቦች ላይ ያተኩራል:- 

  • ደህንነት 
  • እኩልነት 
  • ዘላቂነት 
  • ተንቀሳቃሽነት እና ኢኮኖሚያዊ ወሳኝነት 
  • መኖር የሚያስችል 
  • ጥገና/ በጥሩ ሁኔታ የማቆየት እና ዘመናዊነት 

በ2023 በልግ ውስጥ፣ በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ረቂቅ ላይ የህዝብ ግብረ መልስ ጠይቀናል።  

ይህም ከተማ አቀፍ የመስመር ላይ ተሳትፎን፣ በአካል በመገኘት ዝግጅቶችን መከታተል፣ እና ከጎረቤት ማህበረሰብ ግንኙነት መምሪያ ጋር በመተባበር ለመሥራት ለሚከተሉት ማህበረሰቦች ትኩረት መስጠትን ለማካሄድ ያካትታል:- ጥቁር፣ ተወላጆች እና ሌሎች ባለ ቀለም ሰዎች (BIPOC)፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው፣ አዲስ ሰፋሪ እና ስደተኛ፣ በዕድሜ እየገፉ የመጡ አዋቂዎች፣ ሴቶች፣ የቤት እጦት ወይም የመኖሪያ ቤት አጥተው ድህንነት የሌላቸው ሰዎች፣ እና በአካል ጉዳተኛነት የሚኖሩ ሰዎች።  

ብዙ የመንግስት ሂደቶች በጠረጴዛ ላይ ይከናወናሉበአካልም ሆነ በመስመር ላይ። STP መፍጠር የተለየ ነበር ምክንያቱም የመሳተፍ እድል እንዳለ ለማያውቁ ሰዎች የእኛ ሰራተኞች ጠረጴዛውን ወደ ሕዝብ ለማምጣት ቆርጠዋል። ከመጓጓዣ ፍትሃዊነት ማዕቀፋችን ፈጠራ ዘዴዎችን በመጠቀም፣ እኛ በብዙ አካባቢዎች እና ቋንቋዎች ከተለያዩ ነዋሪዎች፣ የማህበረሰብ አባላት እና የንግድ ድርጅቶች ጋር ከዚህ ቀደም በዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ያልተሳተፉ ውይይቶችን ጠርተናል። ከማህበራዊ ማንነቶች፣ ቋንቋዎች እና ባህላዊ ልምዶች ሁሉ ባሻገር ከማህበረሰብ አባላት ጋር በመገናኘታችን ክብር ተሰምቶናል። እኛ የከተማዋን ስነምህዳር ማክበርን ያካተቱ ጭብጦችን በመስማት፣ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ተጓዦች ደህንነትን በማሻሻል፣ እና ማህበረሰቦችን አንድ ላይ ከማቅረብ ይልቅ ያከፋፍሏቸው የነበሩትን ያለፉ የመጓጓዣ እቅድ ውሳኔዎችን በመጠገን፣ ከከተማችን ተወላጆች እና ስደተኛ ማህበረሰቦች ጋር የትኩረት ቡድኖችን ሰብስበናል/ አነጋግረናል። የሲያትል መጓጓዣ መምሪያ (SDOT) ዳይሬክተር ግሬግ ስፖትስ (Greg Spotts) 

በእቅዱ ላይ ከ1,300 በላይ አስተያየቶችን፣ እና ከ1,000 በላይ በፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ላይ አስተያየቶችን በመስጠት እቅዱን ቅርጽ እንዲኖረው የረዱንን እናመሰግናለን። 

ከሰማናቸው ጥቂቶቹ እነሆ:-  

  • STP የጎላ እና እርምጃ ሊወስድበት ቀላል መሆን ይገባል። 
  • ደህንነት ዋና ትኩረታችን እና ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር መሆን አለበት። 
  • የአየር ንብረት ለውጥን ለመፍታት እንስራ። 
  • መንገዶቻችን እና የህዝብ ቦታዎች ጠንካራ የአካባቢ ኢኮኖሚን እንደሚደግፉ ማረጋገጥ እንፈልጋለን። 
  • መንገዶቻችንን እንዴት እንደምንጠቀም ለመወሰን ሁሉንም ምክንያቶች እና ተቀብሎ መስጠትን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልገናል። 
  • አተገባበሩን ልዩ እናድርገው እና እድገትን እንዴት እንደምንለካ በግልፅ እንግለጽ። 
  • ለመሳተፍ እና ድምጽዎ እንዲሰማ ተጨማሪ እድሎችን ልንሰጥዎ ያስፈልገናል። 
  • አሁን አስቀድሞ ያለንን ነገር በጥሩ ሁኔታ እያቆየን የመጓጓዣ ስርዓታችንን ለማሻሻል እርስዎ ፈጣን ለውጦች እንድናደርግ ይፈልጋሉ። 

በአስፈላጊነት፣ የሲያትል የመጓጓዣ ፕላንን በማዘጋጀት ረገድ ደግሞ ማህበረሰብ መሠረት የሆናቸው አጋር ድርጅቶቻችንን አመራር እና አጋርነት እናመሰግናለን። 

ከዚህ በታች በዚህ ሥራ ውስጥ ማህበረሰብ መሠረት የሆኗቸው ድርጅት አጋሮቻችን ሙሉ ዝርዝር እነሆ:- 

እኛ የማህበረሰብ አስተያየቶችን አዳምጠናል እና በሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ላይ ጥቂት አስፈላጊ ለውጦችን አድርገናል።  

የጨመርናቸው አዳዲስ ቁልፍ ስልቶች እነሆ። 

  • ደህንነት:- የኛ የመጓጓዣ አውታረ መረቦቻችን ጠንካራ እና ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። 
  • ቅጣት አልባ አፈጻጸም:- የትራፊክ ህጎች እንዴት እንደሚተገበሩ ለውጡን እየደገፍን ነው። እኛ ቅጣት ላይ ማተኮር አንፈልግም። ይህ በማህበረሰቦች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እየቀነሰ መንገዶቻችን ደህንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ ይረዳል።  

ሰዎችን እና ዕቃዎችን/ ሸቀጦችን ወደ የሚፈልጉበት ቦታ የማድረስ አስፈላጊነትን ለማጉላት የኢኮኖሚ ወሳኝነትን አስፈላጊነት በመገንዘብ በእንቅስቃሴ ላይ ግባችንን አስፋፍተናል።  

ይህንን የወደፊት ራዕዩን እንዴት ወደ ህይወት እንደምናመጣው የበለጠ ዝርዝር እንዲኖረው ለማድረግ መተግበሪያ ስልታችንን አስፋፍተናል። ቁልፍ እርምጃዎች እንዲከናወኑ ለማገዝ፣ ወደ 30 የሚጠጉ “እርምጃዎችን መተግበር” የተሰኙ ተጨባጭ ድርጊቶችን ጨምረናል። ይህ ክፍል እንዴት ፕሮጀክቶችን እና ፕሮግራሞችን ለመስራት እንዴት እንደምንመርጥ ያብራራል። ባሉ የሀብት/ መረጃ ምንጮች ላይ በመመስረት ስራዎችን እንዴት እንደምናደራጅ እና ለሥራው እንዴት መክፈል ለይተን ማወቅ እንደምንችል እናጋራለን። በመጨረሻም፣ ወደፊት እንዴት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንደምናደርግ በአጭሩ እናቀርባለን። 

በመቀጠልም፣ የከተማው ምክር ቤት እቅዱን እንደራሱ ለማጽደቅ ከግምት ያስገባል። 

በዚህ እቅድ ውስጥ የእርስዎ እና የእርስዎ ጎረቤቶች ድምጽ መንጸባረቃቸውን ማየት እንደሚቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን። 

በቅርቡ መጋቢት 5 በሚደረጉት የከተማው ምክር ቤት የህዝብ አስተያየት ስብሰባዎች ወቅት በመሳተፍ ወይም በጽሁፍ አስተያየቶችን በመላክ፣ ከከተማው ምክር ቤት ጋር መነጋገር/ መገናኘት እና ስለ ሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ድምጽዎን ተሰሚ ማድረግ ይችላሉ። እንዲሁም ለከተማ ምክር ቤት በቀጥታ ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ። አጀንዳው መጋቢት 1 በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ ሲቀርብ እነዚህን ስብሰባዎች እንዴት መቀላቀል እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ። 

አንዴ ከፀደቀ፣ የሲያትል የመጓጓዣ እቅዱ በመደበኛነት የሲያትል ከተማ የመጓጓዣ የወደፊት ራዕይ ይሆናል። 

ከሚለዋወጠው የፋይናንስ ሁኔታዎች፣ የማህበረሰብ ቅድሚያዎች እና ብቅ ባይ መጪ ጉዳዮች ጋር ማስማማት የሚያስችል ማስተካከያዎች ለማድረግ፣ የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ትግበራ በየ 4 አመታት እንዲፈጠር እና እንዲዘመን/ እንዲታደስ ሀሳብ ቀርቧል። የሲያትል የመጓጓዣ እቅድ ትግበራ ፕላን አጠቃላይ ሁሉን አቀፍ ይሆናል እናም ባለፈው ከዚህ ቀደም የተሰሩ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የሕዝብ መጓጓዣ እና የጭነት ትግበራ እቅዶችን ለመተካት የታሰበ ነው። 

ደግሞም ከድጋፍ ገንዘብ ለውጦች ጋር ለማጣጣም የመጓጓዣ የገንዘብ ድጋፍ እቅድ እየሰራን ነው። በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ እቅዱን በምን ያህል ፍጥነት ማከናወን እንደምንችል የድጋፍ ገንዘብ አቅም ይወስናል። 30% የሚያህል የሥራችንን ክፍያ የሚከፍለው የሲያትልን ማንቀሳቀስ (Move Seattle) ቀረጥ በቅርቡ ያበቃል። የቀረጡ ክፍያን ማደስ የሲያትል የመጓጓዣ ስርዓትን ማሻሻል እና በጥሩ ሁኔታ ማቆየት ለመቀጠል፣ የድጋፍ ገንዘብ ምንጭ መኖሩንም ለማረጋገጥ የመጀመሪያ እርምጃችን ይሆናል። በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ ለማወቅ በጥሞና ይጠብቁ!