Find Posts By Topic

ወሳኝ ለሆኑ የጥገና እና ባለበት ሁኔታ እንዲቆይ አስፈላጊ ለሆኑ ስራዎች የባላርድ ድልድይ መጪ የሳምንት መጨረሻ መዘጋት | የቀረጥ ዶላሮች በሥራ ላይ (LEVY DOLLARS AT WORK)  

የባላርድ ድልድይ እይታ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)

ባላርድ ድልድይ በዚህ ቅዳሜና እሁድ፣ ኦክቶበር 4-7፣ 2024 ለተጓዦች ክፍት ይሆናል።

የብሎግ ስታትስቲክስ: 1,200 ቃላት | የ6 ደቂቃ ንባብ 


በጨረፍታ 

  • የ107 አመት ዕድሜ ያለው ድልድይ ላይ የጥገና እና ባለበት እንዲቆይ የጥበቃ ስራን ለማጠናቀቅ ባላርድ ድልድይ በመስከረም እና በጥቅምት በርካታ የሳምንት መጨረሻዎች መዝጋት ያስፈልገናል። 
  • 15th Ave W/NW እና የባላርድ ድልድይ ንጣፍ ሥራ እና ደህንነት ፕሮጀክት (Ballard Bridge Paving & Safety Project) አካል የሆነውን ድልድይ፣ ጠንካራ እና የሚቋቋም እንዲሆን ለማድረግ ያረጁ የማስፋፊያ መገጣጠሚያዎች መተካትን ያካትታል። 
  • የዚህ ብሎግ ልጥፍ የታቀዱ የመዘጋት ቀኖችን በዝርዝር ይገልፃል እና ድልድዩ ተዘግቶ ባለበት ወቅት ለመዘዋወር የድጋፍ ምንጮችን ያቀርባል። 
  • በእነዚህ መዘጋት ወቅቶች ድልድዩ ለእግረኞች እና ብስክሌት ጋላቢዎች ክፍት እንዲሆን እናደርጋለን ብለን እንጠብቃለን። 
  • የባላርድ ድልድይ መዝጋት የጉዞ የእርስዎ ዕቅዶች ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እንገነዘባለን፣ እና የእርስዎን ትዕግስት እና መረዳት እናደንቃለን። 
  • መጪው የድልድዩ መዘጋት በባላርድ ድልድይ ላይ ያለውን በበጋው ወቅት በቅርብ በተጠናቀቀው ሥራ ላይ በመገንባት እያረጀ ያለውን ንጣፍ መተካት ነው። 
  • ከቡድናችን ከሁሉ ይልቅ የቅርብ ጊዜ ዝርዝሮችን ለማግኘት እባክዎትን ለኢሜይል ዝመናዎች መመዝገብዎን ያረጋግጡ። እናመሰግናለን። 

ባላርድ ድልድይ የሚዘጋባቸው ቀናት 

ለአሽከርካሪዎች የታቀዱት ድልድይ መዝጊያዎች እነኚሁና: (ሊለወጥ የሚችል) 

  • ከጥቅምት 11 ቀን 2024፣ ዓርብ ምሽት፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ ጥቅምት 14 ቀን 2024 
  • ከጥቅምት 18 ቀን 2024፣ ዓርብ ምሽት፣ እስከ ሰኞ ጥዋት፣ ጥቅምት 21 ቀን 2024 

የመስመር መዘጋት ቀደም ብሎ አርብ አርብ ከምሽቱ 7 ሰአት ሊጀመር ይችላል፣ ድልድዩ ሙሉ በሙሉ ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ይዘጋል። ድልድዩ እንደገና በሚቀጥለው ሰኞ በግምት ከንጋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል። 

እባክዎን ያስተውሉ: እነዚህ ዕለተ ቀናት እና ሰዓቶች የአየር ሁኔታዎችን፣ የሰራተኞች ቡድን እና የእቃ አቅርቦቶችን መሠረት በማድረግ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ተመስርተው ሊለወጡ ይችላሉ። መረጃን እያገኙ ለመቆየት ለኢሜይል ዝመናዎች እዚህ ይመዝገቡ።   

ተዝግቶ ባለ ወቅት መዘዋወር 

እግረኞች እና የብስክሌት ጋላቢዎች 

  • እግረኞች እና ብስክሌት ጋላቢዎች ባላርድ ድልድይ ለአሽከርካሪዎች ዝግ ሆኖ ሳለ ሊያቋርጡ እንደሚችሉ እንጠብቃለን። 
  • ይህ ለደህንነት ሲባል አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በእግር ለመሄድ እና ብስክሌት ለመጋለብ የአንድ ጎን መንገድ መዝጋት ሊጨምር ይችላል። 
  • እንዲሁም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ለደህንነት ሲባል ከብስክሌቶቻቸው እንዲወርዱ እና በእግር እንዲሄዱ ሊጠየቁ ይችላሉ። 

አሽከርካሪዎች እና ጭነት 

  • ለአሽከርካሪዎች ዋና ቀዳሚ፣ በጣም አስተማማኝ ተቀያሪ መንገድ አውሮራ ድልድይ (SR 99) ነው። 
  • እንዲሁም አሽከርካሪዎች የመርከብ ቦይ (Ship Canal)ን ለመሻገር እንደገና በሌላ ተቀያሪ መንገድ ወደ ዩኒቨርሲቲው ድልድይ ወይም I-5 መቀየር ይችላሉ። 
  • የፍሪሞንት ድልድይ (Fremont Bridge) ክፍት ይሆናል ነገር ግን በአቅም ውስንነት ምክንያት፣ አሽከርካሪዎች ሌሎች ተቀያሪ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እንመክራለን። 
  • በእነዚህ የድልድዮች መዘጋት ወቅት፣ ወደ ሌላ ማዞሪያ የተለጠፉ ምልክቶች አሽከርካሪዎች በመዘጋቱ ወደ ተለዋጭ መስመሮች የመዘዋወሪያ አማራጭ እንዲመሩ ይረዳቸዋል። እንዲሁም ከተቻለ አሽከርካሪዎች ባላርድ ድልድይ አካባቢ ከመድረሳቸው በፊት ወደ ሌሎች መንገዶች እንዲዞሩ እናበረታታለን። 

የመዝጊያ ካርታ 

የመጪው የባላርድ ድልድይ የሳምንት መጨረሻ መዘጋቶችን ቦታ የሚያሳይ ካርታ። ንድፋዊ ምስል: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
የመጪው የባላርድ ድልድይ የሳምንት መጨረሻ መዘጋቶችን ቦታ የሚያሳይ ካርታ። ንድፋዊ ምስል: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT) 

የሕዝብ መጓጓዣ ተሳፋሪዎች  

  • በመደበኛ ባላርድ ድልድይን የሚጠቀሙ አውቶቡሶች በሌላ ማዞሪያ ወደ ፍሬሞንት ድልድይ እንዲሄዱ ስለሚደረግ ረዘም ላለ የአውቶቡስ ጉዞዎች አስቀድመው ያቅዱ። 
  • መዘጊያዎችን ለማገዝ በባላርድ ድልድይ አቅራቢያ ያሉ አንዳንድ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች ለጊዜው ወደ ሌላ ቦታ ሊዛወሩ ይችላሉ። 
  • በአካባቢው ውስጥ ስላለው የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት መረጃ እያገኙ ለመቆየት፣ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የአገልግሎት ምክሮችን ይከተሉ እና ለሕዝብ መጓጓዣ ማስጠንቀቂያዎች/ ማንቂያዎች ይመዝገቡ። 

ጀልባዎች 

  • ጀልባዎች አሁንም በባላርድ ድልድይ ስር ማለፍ ይችላሉ። 

ሌሎች የጉዞ መንገዶች 

ድልድዩ ተዘግቶ ባለበት ወቅት፣ ለመዘዋወር ከታች የተዘረዘሩትን አማራጮች ከግምት ያስገቡ። በአካባቢው ውስጥ መገብየትም ይችላሉ – በግንባታ ወቅት የባለርድ ንግዶች ክፍት ናቸው። እዚህ እነሆ ጥቂት የጉዞ አማራጮች: 

እኛ ድልድዩን መዝጋት ለምን አስፈለገን 

ድልድዮቻችንን መንከባከብ በንቃት አስቀድሞ በመጠገን እና ተጠብቀው እንዳሉ ለማቆየት በተለይም ከመቶ ዓመታት በላይ በፊት ጀምሮ የተሰሩት እንደ ባላርድ ድልድይ ያሉትን ተንቀሳቃሽ ድልድዮችን መንከባከብ አለብን። 16 የተለያዩ የድልድይ ማስፋፊያ መገጣጠሚያዎችን ያካተተ የባለርድ ድልድይ ረጅም ዝርጋታ ላይ በምንሠራበት ጊዜ ሙሉ መዘጋቶች አስፈላጊ ናቸው።  

የማስፋፊያ መገጣጠሚያዎች የድልድይ እንቅስቃሴን እና የሙቀት ለውጦችን ለማስተናገድ የተነደፉ ናቸው። እነርሱም በጣም ጽንፍ የያዘ የአየር ሁኔታ ወይም በትላልቅ የመሬት መንቀጥቀጦች ወቅት ድልድዩ እንዳይጎዳ ለመከላከል ይረዳሉ። 

የማስፋፊያ መገጣጠሚያዎችን መተካት ከነዚህ መገጣጠሚያዎች አጠገብ ያለውን ኮንክሪት ማንሳት ይፈልጋል። የግንባታ ሰራተኞች ቡድን በመገጣጠሚያዎቹ ዙሪያ ያለውን ኮንክሪት በማንሳት እና ደጋፊ የብረት ወራጆችን ሁኔታ መርምረው እንደገና በብረት ያያይዙታል፣ ከዚያም የተበላሹትን የድጋፍ መዋቅር ክፍሎችን ይተካሉ። ከዚያም አዲሱን የማስፋፊያ ማያያዣዎችን ያስገባሉ እና በእነርሱ ዙሪያ አዲስ ኮንክሪት ያፈሳሉ። የመተላለፊያ መንገዱ እንደገና ለትራፊክ ከመከፈቱ በፊት ኮንክሪቱ ቢያንስ 24 ሰአታት ለመጠንከር (ጠንካራ እንዲሆን) ያስፈልገዋል። 

ሌሎች በአቅራቢያ ያሉ ፕሮጀክቶች 

የጉዞ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ በአካባቢው ካሉ ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች ጋር በቅርበት እየተቀናጀን ነው። 

ስለ እያንዳንዱ ፕሮጀክት መረጃ እያገኙ ለመቆየት፣ እባክዎን ከታች ያሉትን አገናኞች ይጠቀሙ: 

የፕሮጀክት መርሃ ግብር 

15th Ave W/NW & Ballard Bridge Paving & Safety Project እና Leary Way Bridge Seismic Retrofit Project ግንባታ የተጀመረው ሐምሌ 2024 ውስጥ ነው እና ሥራው እስከ 2025 መጨረሻ ድረስ እንዲቀጥል ተይዟል። 

በዚህ በጋ የተጠናቀቀው ሥራ እንደገና ሲጠቃለል 

የግንባታ ሰራተኞች ቡድናችን የባላርድ ድልድይ የመጀመሪያ ደረጃ ንጣፍ ስራውን እንደገና ለማጠናቀቅ ጠንክሮ እየሰራ ነበር። የዚህ ሂደት የመጀመሪያ እርምጃ፣ ከተጠበቀው በላይ በከፋ ሁኔታ ላይ የነበረውን የድሮውን አስፋልት ማንሳት ነበር – ከታች ባለው ፎቶ ውስጥ የተሰባበረውን/ የተፈረካከሰውን ንጣፍ ማየት ይችላሉ። የአሮጌው አስፋልት ሁሉም ከዚያ ላይ ከተነሳ በኋላ፣ የግንባታው ሠራተኞች ቡድን አዲስ አስፋልት ለስላሳ ሽፋን በማፍሰስ በድልድዩ ላይ ያሉትን መንገዶች መስመሮች እንደገና ቀለም ቀብተዋል። 

የግንባታ ሰራተኞች ቡድን ከባላርድ ድልድይ ላይ አሮጌውን ንጣፍ ለማንሳት በቡልዶዘር ይጠቀማሉ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
የግንባታ ሰራተኞች ቡድን ከባላርድ ድልድይ ላይ አሮጌውን ንጣፍ ለማንሳት በቡልዶዘር ይጠቀማሉ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
ተሽከርካሪ ለሚነዱ እና ለአውቶቡሱ ተሳፋሪዎች ሰዎች ቀለል ያለ/ ይበልጥ ምቾት ያለው ጉዞን ለመደገፍ፣ የግንባታ ሰራተኞች ቡድን ለባላርድ ድልድይ መንገድ አዲስ አስፋልት ለማፍሰስ ሌሊቱን ሁሉ ይሰራሉ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
ተሽከርካሪ ለሚነዱ እና ለአውቶቡሱ ተሳፋሪዎች ሰዎች ቀለል ያለ/ ይበልጥ ምቾት ያለው ጉዞን ለመደገፍ፣ የግንባታ ሰራተኞች ቡድን ለባላርድ ድልድይ መንገድ አዲስ አስፋልት ለማፍሰስ ሌሊቱን ሁሉ ይሰራሉ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
ወደ ባላርድ ሰፈር እየገባ ያለውን እንደገና የተነጠፈውን ድልድይ እይታ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)
ወደ ባላርድ ሰፈር እየገባ ያለውን እንደገና የተነጠፈውን ድልድይ እይታ። ፎቶ: ሲያትል የመጓጓዣ መምሪያ (SDOT)

በተጨማሪም ከ 15th Ave NW እና NW 56th St. መገጣጠሚያ ጀምሮ የግንባታ ቡድኑ ለእግረኞች፣ የእግረኛ መንገዶችን እና መገናኛዎችን እያሻሻለ ነበር። እየቀጠሉ ሲሄዱ፣ የሰራተኛ ቡድኖች ኮንክሪት እንደገና በመተካት፣ የዛፍ ጉድጓዶችን እያሻሻሉ፣ እና የአቅጣጫ ምልክቶችን እንደገና በመቀባት ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ባላርድ ድልድይ እየሰሩ ነበሩ።

የግንባታ ሠራተኞች ቡድን በ15th Ave NW እና NW 56th St. ላይ ለአዲስ የእግረኛ መንገድ የአስፋልት ንጣፍ በማስቀመጥ እና በማስተካከል የሚያሳይ ፎቶ፡
የግንባታ ሠራተኞች ቡድን በ15th Ave NW እና NW 56th St. ላይ ለአዲስ የእግረኛ መንገድ የአስፋልት ንጣፍ በማስቀመጥ እና በማስተካከል የሚያሳይ ፎቶ፡
በ – ወቅትበኋላ:
የእግረኛ መንገድ ኮንክሪት እንደገና ሲተካ እና በኋላ በ15th Ave NW በኩል ያለው ያው የእግረኛ መንገድ ሁለት ፎቶዎች። ፎቶዎች: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
የእግረኛ መንገድ ኮንክሪት እንደገና ሲተካ እና በኋላ በ15th Ave NW በኩል ያለው ያው የእግረኛ መንገድ ሁለት ፎቶዎች። ፎቶዎች: የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

የእግረኛመንገድኮንክሪትእንደገናሲተካእናበኋላበ15th Ave NW በኩልያለውያውየእግረኛመንገድሁለትፎቶዎች።ፎቶዎች: የሲያትልየማመላለሻመምሪያ (SDOT)

መረጃ እንዳገኙ ይቆዩ