Find Posts By Topic

ወደ ሬኒየር ጎዳና ደቡብ የሚመጡ ቀላል፣ ውጤታማ ጠንካራ የመሃል መስመሮች

A hardened centerline shown in the lower right corner of this photo of an intersection in Portland. Photo Credit: City of Portland

በፖርትላንድ ውስጥ ጠንካራ የሆነ የመሃል መስመር ባለ አንድ መስቀለኛ መንገድ ፎቶ በዚህ በታችኛው ቀኝ ጥግ ላይ የሚታይ።

የፎቶው ሥራ ዕውቅና (Credit) የፖርትላንድ ከተማ

እ.ኤ.አ. በ 2030 ከእንደ ራዕይ ዜሮ (Vision Zero) የግባችን አካል የትራፊክ ሞትን እና ከባድ የአካል ጉዳቶችን ለማቆም ፣ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ በኩል በበርካታ መገናኛዎች ላይ አዲስ “የጠነከሩ የመሃል መስመሮችን” እናስገባለን።

ጠንከር ያሉ የመሃል መስመሮች በእግረኞች መተላለፊያዎች አጠገብ ትናንሽ የጎማ መሰናክሎች ሲሆኑ ሰዎች በመንገድ ላይ አነስ ያሉ ዝመማ እና አራት ማዕዘን ያለው ሆኖ ወደግራ የሚያሽከረክሩትን ቀስ እንዲያደርጉ የሚጠይቁ ናቸው። በሌሎች ከተሞች ውስጥ ይህ ትንሽ ለውጥ የእግረኛ መሸጋገሪያዎች ጋ የተሽከርካሪ ፍጥነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ እና በእግረኛ መሸጋገሪያ ላይ ያሉ ሰዎችን ደህንነት አሻሽሏል። (የበለጠ በእኛ ድረገጽ ጣቢያ ላይ ያንብቡ)።

የምስል መግለጫ፡ የእግረኛ መሻገሪያ አቋርጦ የሚሄድ እግረኛን እና ወደ ግራ በማዞር ላይ ያለ መኪና መደበኛ ባለአራት መንገድ መገናኛውን የሚወክል አንድ የፊት እና ኋላ ስዕል። የፊተኛው ምስል አንድ ሾፌር ያለ ጠንካራ የመሃል መስመር ጣልቃ ገብነት በመስቀለኛ መንገዱ መሃል ላይ በዘዌ ሲያዞር ያሳያል። የኋላው ምስል ጠንከር ያለ የመሃል መስመሩን ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ሾፌሩ ወደቀኝ ማዕዘን መዞሩን ያሳያል።
የምስል መግለጫ፡ የእግረኛ መሻገሪያ አቋርጦ የሚሄድ እግረኛን እና ወደ ግራ በማዞር ላይ ያለ መኪና መደበኛ ባለአራት መንገድ መገናኛውን የሚወክል አንድ የፊት እና ኋላ ስዕል። የፊተኛው ምስል አንድ ሾፌር ያለ ጠንካራ የመሃል መስመር ጣልቃ ገብነት በመስቀለኛ መንገዱ መሃል ላይ በዘዌ ሲያዞር ያሳያል። የኋላው ምስል ጠንከር ያለ የመሃል መስመሩን ጣልቃ ገብነት ለማስቀረት ሾፌሩ ወደቀኝ ማዕዘን መዞሩን ያሳያል።

እነዚህ የት ይሆናሉ?

ለጠንካራ የመሃል መስመሮች ቦታዎችን ስንወስን አንዳንድ ከግምት ያስገባናቸው ነገሮች ከዚህ በታች አሉ።

  • የእግረኞች ጉዳት እና ሞት ታሪክ
  • የተወሰነላቸው የግራ መዞሪያ ደረጃዎች የሌላቸው መገናኛዎች ከትራፊክ ምልክቶች ጋር (ማለትም እግረኞች የመሻገሪያ ምልክት እያላቸው በተመሳሳይ ጊዜ አሽከርካሪዎች አረንጓዴ መብራት አላቸው)
  • ከት/ቤት ወይም ከመጓጓዣ ማዕከል በ ¼ ማይል ውስጥ ማቋረጫዎች
  •  ነዋሪዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እና ከፍተኛ መተማመን በማመላለሻ ላይ ያላቸው አካባቢዎች

በሬኒየር ጎዳና ደቡብ አራት መስቀለኛ መንገዶችን ለደረጃ 1 እናስተናግዳለን፣ በ 2021 ግንባታ ደግሞም 8 ተጨማሪ በ 2022 በደረጃ 2 ጊዜ። የሚቀጥለው ካርታ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ አቅጣጫ ለደረጃ 1 ሰማያዊ እና ለደረጃ 2 በርቱካን ቀለም ቦታዎችን ያሳያል።

የምስል መግለጫ፡ ሬኒየር ጎዳና ደቡብን ጨምሮ የደቡብ ሲያትል ካርታ፣ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ አቅጣጫ 4 መገናኛዎች ለደረጃ 1 ግንባታ ተብሎ የተሰየመ እና 10 መስቀለኛ መንገድ ደረጃ 2 ግንባታ የተሰየመበት። የተመረጡ መገናኛዎች ከደቡብ ማሳቹሴትስ መንገድ እስከ ደቡብ ኦቴሎ መንገድ ድረስ ወደ ሰሜን ይጓዛሉ።

በሚከተሉት መገናኛዎች ላይ ጠንካራ የመሃል መስመሮችን ለማስገባት አቅደናል

ደረጃ I

  • Rainier Ave S & S Massachusetts St 
  • Rainier Ave S & S Charlestown St 
  • Rainier Ave S & S Edmunds St 
  • Rainier Ave S & S Graham St

ደረጃ II

  • Rainier Ave S & S Bayview St 
  • Rainier Ave S & S Walden St 
  • Rainier Ave S & S Andover St 
  • Rainier Ave S & S Genesee St
  • Rainier Ave S & S Alaska St
  • Rainier Ave S & S Ferdinand St 
  • Rainier Ave S & S Hudson St 
  • Rainier Ave S & S Orcas St 
  • Rainier Ave S & S Holly St 
  • Rainier Ave S & S Othello St

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ ከሠራናቸው በርካታ የሥራ እቅዶች አንዱ ይህ ነው። በዚህ በተጨናነቀ ጠባብ መተላለፊያ ሰዎች እንዲራመዱ፣ እንዲንሸረሸሩ፣ ቢስክሌት እንዲነዱ፣ መኪና እንዲያንሸረሽሩ እና የመጓጓዣ መውሰድ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እንደ ራዕይ ዜሮ (Vision Zero) መርሃ ግብራችንየተለያዩ የደህንነት ማሻሻያዎችን አጠናቅቀናል

እ.ኤ.አ. በ 2015 በደቡብ አላስካ መንገድ እና በደቡብ ኬኒ መንገድ መካከል አንድ ማይል ሬኒየርን ከ 4 ወደ 3 መስመሮች እንደገና ቀይሰናል። ይህ የሥራ እቅድ ኮሎምቢያ ከተማ እና ህልማን ከተማ ውስጥ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ በኩል ደህንነትን በተሳካ ሁኔታ አሻሽሏል። በዚያ ስኬት ላይ በመገንባት፣ በ 2017 በሂልማን ከተማ እና በሬኒየር ውሃ ዳርቻ መካከል የሥራ እቅዱን ሁለተኛ ምዕራፍ ጀመርን። እ.ኤ.አ. በ 2019፣ በመስቀለኛ መንገድ ማሻሻያዎችን አድርገን እና በአካባቢው በተወሰኑ ቦታዎች የአውቶቡስ መስመሮችን ጨመርን። ባለፈው ዓመት የማህበረሰብ የእግረኛ መሻገሪያን ጨምሮ በበርካታ ተጨማሪ መገናኛዎች ላይ ማሻሻያዎችን አድርገናል ፣ እና ከደቡብ ኬኒ መንገድ እስከ ደቡብ ሄንደርሰን መንገድ አዲስ የመንገድ አቀማመጥ አጠናቀናል።

 ቀጥሎስ ምንድነው? በሚቀጥሉት በርካታ ወራት ውስጥ ጠንካራ የሆኑ የመሃል መስመሮችን እናስገባለን። ግባችን እስከ ፀደይ 2022 ድረስ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ በሁሉም አካባቢዎች ማስገባቱን ማጠናቀቅ ነው።

እየተራመዱ፣ የሚንሸረሸሩ፣ ብስክሌት የሚነዱ ወይም መኪና የሚያሽከረክሩም ቢሆኑ፣ በሬኒየር ጎዳና ደቡብ በኩል የሚገኙ አዲስ ጠንካራ የሆኑ የመሃል መስመሮችን ይጠብቁ!

በጠንካራ የመሃል መስመሮች እና እንዴት ሬይኒር ጎዳና ደቡብ ለእግረኞች የበለጠ ደህንነቱን የተጠበቀ እያደረግን እንዳለ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን የምስጢር ምልክት (code) ከስማርትፎንዎ ጋር ይቃኙ!