Find Posts By Topic

የሚቀጥለው ለእኛ የ”ደህና ጅማሮ” (“Safe Start”) ከቤት ውጭ መመገቢያ እና የጠርዝ ቦታ ያለው የፍቃድ አጠቃቀም ፕሮግራም ምንድን ነው?


Please note: to return to the English version of this blog, you can click here.


Outdoor dining and coffee-sipping space in Seattle’s Capitol Hill neighborhood. A person can be seen sitting while drinking a coffee, as another person walks down the sidewalk.
Outdoor dining and coffee-sipping space in Seattle’s Capitol Hill neighborhood. Photo credit: SDOT

በሰኔ 2020 ውስጥ፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሲያትል ምግብ ቤቶችን፣ የምግብ አቅራቢዎችን እና የችርቻሮ ንግድ ሥራዎችን ለመርዳት ጊዜያዊ የ ደህና ጅማሮ (Safe Start) ፕሮግራም ፈጠርን። የደህና ጅማሮ ፕሮግራም ለንግድ ድርጅቶች የመንገድ እና የእግረኛ መንገድን ለመጠቀም ፍቃድ እንዲያገኙ ቀላል አድርጎታል። ይህም በወረርሽኙ ወቅት በደህንነት መሥራት የሚያስችል ተጨማሪ ቦታ እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል።

ፕሮግራሙ ከቤት ውጭ መመገቢያ፣ መሸጫ፣ የሸቀጣሸቀጥ ማሳያዎች እና የመንገድ መዘጋት አማራጮችን ያካትታል። በደህና ጅማሮ ፕሮግራም ሥር ከ275 በላይ ፈቃዶችን ሰጥተናል። ጥር 31 ቀን 2023 ጊዜው እንዲያበቃ ተደርጓል። ይህንን ቅጥያ ስናስታውቅ በየካቲት ወር በብሎግ ልኡክ ጽሁፋችን ላይ የበለጠ ማንበብ ይችላሉ።

ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ወደ 380 የሚጠጉ የውጪ የመመገቢያ ፈቃዶች፣ 20 የሸቀጣሸቀጥ ማሳያዎች እና 180 የሽያጭ ፈቃዶች ነበሩ። አብዛኛዎቹ ደህና ጅማሮ (Safe Start) ፈቃዶች ለቤት ውጭ መመገቢያ ናቸው፣ እና ከ60% በላይ የሚሆኑ ፈቃዶች በመንገዱ ጠርዝ ቦታ ውስጥ ናቸው።

በከተማው ውስጥ ለካፌዎች፣ ለሽያጭ እና ለሌሎች የማህበረሰብ እና ለንግድ አላማዎች የሚያገለግል የመንገድ ጠርዝ ቦታ የአንድ ኪነ ጥበብ አገላለጽ። ስዕላዊ ገለጻ: ቆስጠንጢኖስ ክርሳፊስ (Constantine Chrisafis)፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)
በከተማው ውስጥ ለካፌዎች፣ ለሽያጭ እና ለሌሎች የማህበረሰብ እና ለንግድ አላማዎች የሚያገለግል የመንገድ ጠርዝ ቦታ የአንድ ኪነ ጥበብ አገላለጽ። ስዕላዊ ገለጻ: ቆስጠንጢኖስ ክርሳፊስ (Constantine Chrisafis)፣ የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT)

በፈቃድ መስፈርቶቻችን ላይ የረጅም ጊዜ ለውጦችን እና ዝመናዎችን የሚያካትት አንድ ረቂቅ የሃሳብ አቅርቦትን ፈጠረናል። ከጸደቀ፣ የድህና ጅማሮ (Safe Start) አንዴ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ካለቀ በኋላ እነዚህን ለውጦች ወደ ተግባር እናውለዋለን። የሚቀርበውን ሃሳባችንን በዚህ ክረምት ለማጠናቀቅ እናቅዳለን። የቀረቡ ሃሳቦች ላይ መሰረታዊ ነገሮችን ከታች በታች ማግኘት ይችላሉ።

ከቤት ውጪ መመገቢያ

የእኛ የቀረበ ሃሳብ ረቂቅ በወረርሽኙ ወቅት የታዩትን ብዙዎች ስኬቶችን ይቀጥላል። በሁለቱም በእግረኛው መንገድ ዳርቻዎች እና በመንገዱ ጠርዝ ቦታ ውስጥ ከተቋማቸው ጋር ለቤት ውጭ መመገቢያ መፍቀድ እንቀጥላለን። መጥፎ የአየር ሁኔታን ለመቋቋም አንዳንድ ተቋሞች መቀየር ወይም ማጠናከር ሊኖርባቸው ይችላል። እንዲሁም አንድ አዲስ፣ ወቅታዊ ፍቃድ በማቅረብ ለምግብ ቤቶች እድሎችን እናሰፋለን። ይህ ፈቃድ ከሚያዝያ እስከ ጥቅምት ድረስ የሚሰራ ይሆናል። ለንግዶች በሞቃቱ ወራት ውስጥ ከቤት ውጭ መመገቢያ ክፍት መሆናቸው ተስማሚ ነው።

ስለቀረቡት ከቤት ውጪ መመገቢያ ሃሳብ ለውጦች መረጃ የእኛን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ።

የሸቀጣ ሸቀጦች ማሳያዎች

የእኛ የሃሳብ አቅርቦት የችርቻሮ ንግዶች ከመደብራቸው ፊት ለፊት ሸቀጣ ሸቀጦችን እንዲያስተዋውቁ ይፈቅድላቸዋል። ይህ ለፈቃድ የማመልከት አስፈላጊነትን ያስወግዳል።

ነፃነቱ በእያንዳንዱ ማሳያ ላይ አይተገበርም። ከሱቆቻቸው አጠገብ የእግረኛ መንገድ ጠርዝ ላይ ወይም ከህንፃቸው አጠገብ በቀጥታ ከንግድ ስራቸው በስተውጪ ከመደብራቸው አጠገብ የችርቻሮ ማሳያዎችን ማስቀመጥ የሚፈልጉ የሸቀጣ ሸቀጦች ንግዶች ማሳያቸው ለተፈጠሩት መደበኛ መስፈርቶች ከፍቃድ-ነፃ አማራጭ የማያሟላ ከሆነ አሁንም ፍቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ንግዶች ለረጅም ጊዜ እና ለወቅታዊ ፈቃዶች ማመልከት ይችላሉ። የረጅም ጊዜ ፈቃዶች በየዓመቱ ይታደሳሉ። ወቅታዊ ፈቃዶች ከሚያዝያ እስከ ጥቅምት ድረስ የሚሰሩ ናቸው። 

  • ከንግዲህ ወዲህ በመንገድ ጠርዝ ቦታ ላይ ለሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያዎች ምርጫ አንሰጥም። እነዚህ ማሳያዎች ሌሎች በአስተማማኝ ጅማሮ ፕሮግራም ስር ካሉ የመንገድ ጠርዝ ቦታ አጠቃቀሞች ጋር ሲነፃፀሩ ዝቅተኛ የፍላጎት ጥያቄ አላቸው። መንገዶች ሲዘጉ ወይም ለሌላ ጊዜያዊ ለተፈቀዱ ክስተቶች ልዩ የሆኑ ሁኔታዎች አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላሉ። 

ለሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያ ስለቀረቡት የሃሳብ አቅርቦት ለውጦች መረጃ የእኛን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ።

መሸጥ

የእኛ የመንገድ እና የእግረኛ መንገድ የሽያጭ ፕሮግራማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። ለአዳዲስ እና ለተቋቋሙ አነስተኛ ንግዶች የተረጋጋ እድሎችን ይሰጣል። አብዛኛውን የሽያጭ ፈቃዶቻችንን ለ12 ወራት ነው የምንሰጠው።  

ከወረርሽኙ በፊት ለአዳዲስ አቅራቢዎች እድሎችን መጨመር ፈታኝ ነበር። አንድ ላልተረጋገጠ፣ አዲስ ለሆነ ጣቢያ የአንድ ሙሉ ዓመት ቁርጠኝነት መስጠት፣ በተለይም በውስን የሀብት ምንጮች ላይ ከባድ ሊሆን ይችላል።  ይህንን ችግር ለመፍታት አንድ የሶስት-ወር የሙከራ ፍቃድ አዋኅደናል። የፈቃዱን የጊዜ ገደብ እና የተቀነሰ ወጪ አቅራቢዎች አዳዲስ ቦታዎችን ለመሞከር የሚያደርጉትን ጥረት ይደግፋል። ሀሳቡ በ2021 በአንድ አነስተኛ የአቅራቢዎች አማካሪ ቡድን ውስጥ ከተሳተፉ ሻጮች የመጣ ነው።

የሽያጭ ዓይነቶችን፣ የአቅራቢዎችን ብዛት እና የወረዳ ክፍፍልን ውስንነቶች በማስወገድ ተጨማሪ የሽያጭ እድሎችን እየፈጠርን ነው።

ለመንገድ ዳር አሻሻጥ ስለቀረቡት የሃሳብ አቅርቦት ለውጦች መረጃ የእኛን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ።

የመንገድ እና የእግረኛ መንገድ እንቅስቃሴዎች

የእኛ የመንገድ እና የእግረኛ መንገድ እንቅስቃሴ ፈቃዶች ተቋማትን፣ የማህበረሰብ ቡድኖችን እና ድርጅቶችን መንገዶቻችንን፣ ሰርጦችን እና አደባባዮችን እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል። ለእነዚህ ቦታዎች ሕይወት በመስጠት፣ እነዚህ እንቅስቃሴዎች የእኛ ማህበረሰብ ስሜታችንን ያጠናክራሉ። በወረርሽኙ ወቅት፣ እነዚህ ፈቃዶች ደንበኞችን ለማገልገል ለምግብ ቤቶች እና ለችርቻሮ መሸጫ መደብሮች የተጨማሪ ቦታዎች መጠቀሚያ ነበሩ። ማህበረሰቦቻችን ከወረርሽኙ ጋር እየተላመዱ ሲሄዱ፣ እንደገና ብዙ አይነት እንቅስቃሴዎችን ለማካተት እነዚህ ፈቃዶች ይሰፋሉ። 
ስለመንገድ እና ለእግረኛ መንገድ ክስተቶች ስለቀረቡት የሃሳብ አቅርቦት ለውጦች መረጃ የእኛን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ።

ክፍያዎች

በጊዜያዊ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፕሮግራም በኩል ለሚሰጡ ፈቃዶች ምንም የፍቃድ ክፍያዎች የሉም። ወረርሽኙ የእለት ተእለት ህይወታችንን እንዳስተጓጐለ አላማችን ማህበረሰቦቻችንን መደገፍ ነበር። የጊዜያዊ ፕሮግራሙ አንዴ ካለቀ በኋላ፣ ለእነዚህ የፈቃድ ዓይነቶች ክፍያዎችን ማስከፈል እንቀጥላለን።

በ2020 የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፕሮግራምን ካስታወቅን በኋላ ስለምናገለግላቸው ንግዶች ብዙ ተምረናል። የሰራተኞቻቸውን ፍላጎት እና አዋጭነታቸውን ጊዜያዊ እና የረዥም-ጊዜ ሚዛን ለመጠበቅ ጠንክረው ሲሰሩ ተመልክተናል። በከፍተኛነት እርግጠኛ ባልሆኑ እና አስቸጋሪ ጊዜያት የሀገር ውስጥ የንግድ ባለቤቶች የተሰሉ የአደጋ ስጋቶችን ሲወስዱ፣ ሃሳቦችን እና እቅዶችን ሲጋሩ፣ አንዳቸው የሌላውን ፈጠራ እና አዲስ ለውጦች ላይ ሲገነቡ እና አብረው ሲሰሩ አይተናል። በአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፍቃዶች የተፈጠሩትን እድሎች በሚገባ ተጠቅመውበታል እና ለዚህ አጋዥ ፕሮግራም ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የ2023 ክፍያዎችንን በተማርነው ላይ ለመገንባት እና ቁልፍ የተገመቱ ጉዳዮችን ለመፍታት ወስነናል:

  • ለአነስተኛ የንግድ ሥራ ባለቤቶች እና የማህበረሰብ ድርጅቶች በዋጋ ተመጣጣኝ መሆን አለበት። ማህበረሰቦቻችንን እንደገና ስንገነባ የንግድ አጋሮቻችንን መርዳታችንን መቀጠል እንፈልጋለን። እንዲሁም በፕሮግራማችን ውስጥ እኩልነትን ማዕከል ማድረግ እንፈልጋለን።
  • ወጪዎቻችንን በፍቃድ ዋስትና አሰጣጥ፣ በእድሳት እና በማሻሻያ ክፍያዎች ማስመለስ አለብን። ይህ ሰራተኞቻችን ማመልከቻዎችን ሲገመግሙ እና ፈቃዶችን በሚሰጡበት ጊዜ ለሚያከናውኗቸው ሥራ በተሻለ ሁኔታ ክፍያዎችን ያቆራኛል። በተጨማሪም የረጅም-ጊዜ የፕሮግራም ዘላቂነትን ያረጋግጣል።
  • በተቻለ መጠን ቀላል መሆን አለበት። ይህ የተጠቃሚ-ምቹነትን ይጨምራል እና ውጤታማ ሂደትን ይረዳል።
  • እሴቶቻችንን መወከል ይኖርበታል። የህዝብ ከፍት ቦታ አጠቃቀምን ማበረታታት እንፈልጋለን። ይህንን ለማድረግ፣ በኛ የሃሳብ አቅርቦታችን የዋጋ ተመጣጣኝነት እያሻሻልን ፕሮግራሙን ለማስቀጠል የፈቃድ ክፍያዎችን ማስተካከል እንችላለን።


ስለቀረቡት የክፍያዎች ሃሳብ ዝርዝሮችን ለማየት እነዚህን ልዩ ገጾች ይመልከቱ:

ቀጥሎስ ምንድነው?

ከእርስዎ ግብረ መልስ ለማግኘት ይህን ረቂቅ እቅድ እየተጋራን ነው። ስለዚህ የሃሳብ አቅርቦት የመጨረሻ እትም ለመድረስ በምንሰራበት ወቅት ስለእቅዶቻችን ግንዛቤ ማሳደግ እንፈልጋለን። በዚህ ክረምት ወደኋላው ላይ የመጨረሻ የሃሳብ አቅርቦታችንን ለከተማ ምክር ቤት ለማቅረብ አቅደናል። ማንኛውም ግብረመልስ ቢኖርዎት፣ ጥያቄዎች ወይም የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ፣ እባክዎን በ publicspace@seattle.gov ላይ ኢሜይል ያድርጉልን። እንዲሁም የእኛን ድህረ-ገጽ በማንኛውም ጊዜ መጎብኘት ይችላሉ።

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች:

ጥያቄ ፡ የአሁኑ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ካፌ አለኝ። ተመሳሳይ መጠን ያለው ካፌ ማቆየት እችላለሁ?

መልስ: ያ እንደሁኔታው ይወሰናል። ካፌዎ ከ40 ጫማ በላይ ርዝማኔ ካለው፣ ትንሽ ከዚህ ያነሰ መሆን ይኖርበት ይሆናል። ይህም ተሽከርካሪ ጭነት የሚጭንበት እና ማራገፊያ ቦታ መኖሩን ማረጋገጥ እንድንችል ነው። እንዲሁም የአጎራባች ንግድ ሥራ የመንገዱን ጠርዝ ቦታ ወይም የእግረኛ መንገዱን መጠቀም እንደሚችል ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ነገር ግን፣ ከ40 ጫማ በላይ የሚረዝሙ ካፌዎች ሳይለወጡ የሚቀሩባቸው ብዙ አጋጣሚዎች ይኖራሉ።

ጥያቄ: እኔ አሁን ያለኝ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ካፌ ከጣሪያ መዋቅር ጋር ነው። ማቆየት እችላለሁ?

መልስ: እንደገና፣ ያ እንደሁኔታው ይወሰናል! ሰዎችን ከሲያትል ዝናብ እና (አልፎ አልፎ) ጸሀይ እንዲከላከሉ ከላይ በኩል የተዋቀሩትን መፍቀድ በመቀጠላችን ደስተኞች ነን። ይሁን እንጂ፣ አወቃቀሩ የበለጠ ጠንካራ ወይም ክብደት የተሰጠው ሊሆን ይችላል። ይህ ከፍተኛ ንፋስ በሚኖርበት ጊዜ በቦታው እንዲቆይ ይረዳል።

ጥያቄ: የኔ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ካፌ ወይም የውጪ ሸቀጣ ሸቀጥ ማሳያ ሰዎችን ከዝናብ እና ከፀሀይ ለመጠበቅ ድንኳን ይጠቀማል። ያንን አማራጭ መፍቀዱን ይቀጥላሉ?

መልስ: አዎ! ፕሮግራማችን ሰዎችን ከዝናብ እና ከፀሀይ ለመጠበቅ ብቅ የሚሉ ድንኳኖች መፍቀዱን ይቀጥላል። የምንጠይቀው አውሎ ንፋስ ሊሆን ሲጠበቅ ድንኳኑን እንዲያነሱት ብቻ ነው።

ጥያቄ: ስለ መብራትና ማሞቂያስ? እነዚያን በቦታቸው ማቆየት እችላለሁ?

መልስ: እንደገና፣ እንደሁኔታው ይወሰናል። እነዚህ ቦታዎች ምቹ ሆነው መቆየታቸውን ማረጋገጥ እንፈልጋለን፣ ይህም ብዙውን ጊዜ ሙቀት እና መብራት እንዲኖራቸው ማለት ነው። አንዳንድ የተለመዱ የማሞቂያ መሠረታዊ ነገሮች፣ እንደ ረጅም “የእንጉዳይ ዘይቤ” ቀለም የለሽ የጋስ ማሞቂያዎች፣ የሚፈቀዱት ጣሪያ ወይም ሽፋን ከሌለ ብቻ ነው። ሌላ፣ ትንሽ ቀለም የለሽ የጋስ ማሞቂያዎች በሽፋን ስር ቢሆን እንኳን ይፈቀዳሉ። መብራቶች ከሕንጻ ኮድ ጋር መስማማት ብቻ ያስፈልጋቸዋል፣ እና እንደሱ ከሆነ ይፈቀዳሉ።

ጥያቄ: የአሁኑ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፍቃድ አለኝ። እንደገና ማመልከት ይኖርብኛል?

መልስ: አዎ፣ በተሻሻለው የፍቃድ አይነት እንደገና ማመልከት ያስፈልግዎታል። የእኛ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፕሮግራማችን በጣም የተነደፈው እንደ ድንገተኛ ወረርሽኝ ምላሽ ነው። የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፕሮግራም በነባር የፍቃድ አማራጮች ላይ የተመሰረተ ነበር። እነዚህን ነባር የፈቃድ አማራጮች እያዘመንን ነው እና ከአሁን በኋላ የአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) ፈቃዶችን አንሰጥም። በተዘመነው የፈቃድ አይነቶች፣ እኛ የርስዎን ካፌ አንድ ጠለቅ ያለ ግምገማ እያደረግን መሆኑን እና የምንፈልገውን ውሂብ እንዳለን ማረጋገጥ አለብን። ካፌዎ በአስተማማኝ ጅማሮ (Safe Start) (ወይም ባይሆንም እንኳ) ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ከሆነ ፈቃድዎን ለማጽደቅ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፣ ነገር ግን አንዳንድ ለውጦችን ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል።